ዛሬ ዛሬ ሙስሊሟን ሴት የእመቤትነት ማእረግ ሊያስጥሏት የሚፈለፈሉ ፈተናዎች ተበራክተዋል። ለአማኟ ሴት ትላንት ቤቷ ውስጥ እንድትረጋ የተላለፈው ኢስላማዊ ድንጋጌ መውጣቷን ተከትሎ ብዙ ችግሮች ስለሚከሰቱ ነበር። ዛሬ ግን መልኩን ቀይሮ በመጣው ፊትና facebook skype paltalk whatsapp እና የመሳሰሉት ጥፋት የሚበዛባቸው መስኮቶች ላይ አማኟ ሳታውቀው እንዲያውም በአላም ላይ አካላይ ሆና ተገኝታለች። መቼም እንደዚህ ስል ወይ ጉድ የሚጠቅም ጎን የለውም ነው የምትይው???” የሚሉ ጥያቄዎች ስፍር ቁጥር እንደማይኖራቸው እገምታለው ይሁን እሺ ኸይር እንደማመጥ! ጥቅም እንዳለው ባይካድም የጥፋት ጎኑ ግን የደለበ ነው። በእርግጥ እንደሰውየው አጠቃቀምም የሚወሰንበት ሁኔታ አለ። ለማንኛውም ግን በሴቷ ላይ የሚያደርሰው ጥፋት ከባድ ነው። አዎ! በእርግጠኝነት አንድ ሙስሊም ሴት ምንም የባሰባት ብትሆንም ከቤት ወጥታ በምታደርገው ጉዞዋ ላይ የምታውቀውንም የማታውቀውንም ባእድ (አጅነብይ) ወንድ ቆማ ከሰላምታ አልፎ የባጡን የቋጡን የምትዛላብድ አልነበረችም። ባልተፈቀደ መንገድ የወንድ ጓደኛ በመያዝ የተፈተነች እንኳ እንደው የለየላት ካልሆነች በስተቀር ጓደኛዋን ለማውጋት እንኳ ቦታና ሁኔታዎችን በመምረጥ ትሽሽግ ትሰወር ነበር። ዛሬ ዛሬ ግን ነገር አለሙ በቀለለና በተራቀቀ መልኩ ከተፍ ያለላት ትመስላለች። እንደትላንቱ ብዙ ውጣ ውረድ አያስፈልጋትም። በመሆኑም ትላንት እንኳ እርቃን በሆነችበት ጊዜ ያልደፈረችውን ዛሬ በቤቷ ተቀምጣ online ወደ ሚባለው የጥፋት ቦታ በየቀኑ በየሰአቱ እየተገኘች አለም አቀፍ ወንዶችን ትፈትናለች ታማልላለች። ትላንት በመንገድ ሲለክፏት እንኳ የምትሽኮረመም አሊያ ምን ሲደረግ ተነክቼ በሚል የነብር አራስ ትሆን የነበረችው ዛሬ ዛሬ ግን ምስሏን (በሂጃብም ቢሆን) በመልቀቅ በ comment አማካኝነት የሚመጡ ለከፋዎችን በደስታ በፌሽታ እያጣጣመችው ትገኛለች። “ተገላቢጦሽ” ማለት እንግዲህ ይሄ ነው። አሁንም ጥያቄ ተነስቷል። “እንዴ ጭራሽ online አትሁኑ ነው እንዴ የምትይን???” አይደለም። ነገር ግን አስፈላጊ ሲሆን ብቻ ነው መሆን የሚገባው። ለነገሩ ሳይሆኑም አስፈላጊ ነገሮች መሰራት ይችላሉ። post ማድረግ ትችያለሽ። like ማድረግ ትችያለሽ። comment መስጠት ትችያለሽ። ማንበብ ማድመጥ መፃፃፍ ሌላም ሌላም ትችያለሽ። እንግዲህ ይህ ከሆነ ለምን ታዲያ ሃያ አራት ሰአት online መሆን ተፈለገ??? መልሱን እራሷን መሸንገል ለማያውቃት እንቁዋ አማኝ እህቴ ትቼዋለው። ሌላው ችግር ደግሞ ብዙዎቻችን ላፕቶፑን አሊያ ሞባይሉንና ወዘተ ብቻ አይደለም online የምናደርገው። ይልቁንም እኛም ጭምር ነን on የምንሆነው። አላሁል ሙስተዓን። በእውነቱ ይህን መሰል የጥፋት ቦታ ላይ አማኝ ሴት ነቃ ልትል ይገባል። የውስጥም ይሁን የላይ ጠላቶቿ ኢስላም የቸራትን ማእረግ ለማስጣል የማይቆፍሩት ጉድጓድ እንደሌለ በወጉ ልትገነዘብ ይገባል። እነዚህንም መሳሪያዎች መጠቀም ካለባትም ተጠቅማ ልትጠቅምበት በምትችለው ነገር ላይ ብቻ ልታውለው ይጋባል። የበለጠ አላህን ልትፈራበት፤ ምንም ነገር የማይደበቅበትን ተቆጣጣሪነቱን ለአፍታም ቢሆን የማትዘነጋበት ሊሆን ግድ ይላታል። ይገርማል ጥያቄዎች እንደቀጠሉ ናቸው። “እሺ እኛ ብቻ ነን እንዴ ጥፋተኞች ወንዶቹስ???” አልወጣኝም።
ነገር ግን ይህን ጥያቄ ከመመለሴ በፊት፦ ለጥፋት መንሰኤ በመሆንና ጥፋተኛ በመሆን መካከል ያለው የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ሊጤን ይገባዋል እላለሁ። አሊያ ደግሞ በሌላ አነጋገር እኛ በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው በየሴኮንዱ online እየዋልን። በጎን ደግሞ የchat መስኮት አጣድፎ ገደለን ብንል እንዴት ነው ተቀባይነቱ የሰፋ ሊሆን የሚችለው??። ለምንስ ነው በቂ ምክንያት ሳይኖረን ወንዶችን የምናናግረው??። አዎ ብዙ ጊዜ ጀማሪዎቹ ወንዶች እንደሆኑ ይገባኛል። ግና ቀጣዮቹና ጨራሾቹ እኛ ከሆንን የጥፋቱን መጠን መገመት አያዳግትም። ጥፋትን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ባይቻል ራሱ መቀነስ ግን ይቻላል። አስፈላጊ ካልሆነ profile ዝርዝር መረጃን ግልፅ አለማድረግ። እንዲሁም በስም ከመግባት መቆጠብ። ሁሉ ነገር ልክ ሲኖረው ነው ሚበጀው። ያለ ጥርጥር በእንደዚህ አይነቶች የመገናኛ ብዙሃን ላይ ያለው የወንዶች እይታም ለከት ሊኖረው ይገባል። አላህን ሊፈሩበት የግድ ነው። አሁን አሁንማ አላህ ያዘነለት ሲቀር እነዚህን መሳሪያዎች መጀናጀኛ እና መተጫጫ ያደረጉት ለቁጥር ታክተዋል። በዚህ መልኩ ለትዳር የመብቃት ስምረትን ሙሉ በሙሉ ማስተባበል ባልደፍርም ባብዛኛው ግን ከንቱ ድካም ነው። ስንትና ስንት ሴቶች ናቸው እውነተኛ ማንነታቸውን ሳታውቅ በጉጉት የሚያዋዥቁህ። ወይ ብቸኝነትህን እንዳታስታም አሊያ ትዳርህን እንዳታጣጥም ውጋት የሆኑብህ። ወንድሜ አላህን ልትፈራ ይገባል።
ኡስታዛ ኡሙ ዐብደላህ ነፊሳ ሙሀመድ
No comments:
Post a Comment