Wednesday, 27 January 2016

PART 3 የእንስቶች ወርሃዊው ዙር

 በመቀጠል የኢስቲሃዳ ደምን ከሀይድ ደም በምን መልኩ መለየት እንደምንችል እንመለከታለን።

 የወር አበባን ደም ከኢስቲሃዳ  ደም መለያ 4ቱ ወሳኝ ነጥቦች

①         1ኛ ቀለም اللون
y የሀይድ (የወር አበባ) ደም ቀለሙ
     ጥቁር (ጠቆር ያለ) ሲሆን
yየኢስቲሃዳ ደም ቀለም ደግሞ
    ቀይ (ቀላ ያለ) ነው።
②          2ኛ   ቅጥነት  الرقة
yየወር አበባ (የሀይድ) ደም ወፈር
     ያለ ሲሆን
yየኢስቲሃዳ ደም ግን ቀጠን ያለ
      ነው።                    
3ኛጠረን (ሽታ)  الرائحة:
yየሀይድ (የወር አበባ) ደም ሽታው ጥሩ ያልሆነ ጠረን ሲኖረው
yየኢስቲሃዳ ደም ግን መጥፎ ሽታ የለውም። ምክንያቱም ከደምስር የሚወጣ የተለመደው የደም አይነት ነውና።
          4ኛየመርጋት ሁኔታ التجمد
y የወር አበባ (የሀይድ) ደም ከፈሰሰ ወይም ከታየ በኋላ አይረጋም።
y የኢስቲሃዳ ደም ግን ከደምስር በመሆኑ ከፈሰሰ በኋላ ይረጋል።
   ጠቅለል ሲል በነዚህ ዋና እና መሰረታዊ መለያዎች የሀይድን ደም ከኢስቲሃዳ ደም ለይተው ማወቅ: ይችላሉ። በዚህም ለዒባዳዎም ሆነ ተያያዥ ለሆኑት ሙኣመላዎች ራስዎን ያዘጋጃሉ።

ከሀይድ ደም ቀለም ውጭ ሌላም አይነት ቀለም ያለው ፈሳሽ
           ምን ይሆን

 ቢጫማ ወይም ቡናማ ፈሳሽ ይህ ፈሳሽ በብዙሃን እንስቶች ላይ የወር አበባቸውን በታከከ በተለይ በሶስት ዋና ዋና ጊዜያት ሊከሰት ይችላል ።
① ከሀይዷ (ከወር አበባዋ) መምጣት አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀድሞ የሚከሰት
② ከሀይድ ከመንፃቷ በፊት ከፍሰቱ በኋላ መጨረሻ ላይ የሚከሰት የሀይድ ፍሰት አብቅቶ ከጠራች በኋላ የሚከሰቱ ናቸው።
የመጀመርያው
        الصفرة أو الكدرة قبل الحيض
ከሀይድ በስተፊት ቢጫማ ወይም ቡናማ ቀለም ያለው ፈሳሽ ከፈሰሳት         
    ይህ ፈሳሽ በተለምዶ በወር አበባ መምጫ ግዜዋ በሀይድ ላይ በምትሆንበት ወቅት ወይም
yበጥቂት ቀናት ቀድም ብሎና
yከሀይድ ህመም ወይም ቁርጠት
    ጋር ተጎዳኝቶ ከመጣ ከዚያም
yይህንንም ፈሳሽ ተከትሎ የሀይድ ደም ከፈሰሳት ይህ የሀይዷ (የወር አበባዋ) ባህሪና ሀይዷ ራሱ በመሆኑ:-
👉 በዚህ ወቅት ከሰላትም ከፆምም  ትታቀባለች ። ይህም ማለት ይህ ቢጫ ወይም ቡናማ ፈሳሽ ከሀይድ (ከወር አበባ) ደም በአንድ ወይም በሁለት ቀናት ቀድሞ ከሀይድ ህመም (ቁርጠት) ጋር ከመጣና
y ሀይዱም በሶስተኛው ቀን ከፈሰሳት ሁሉም በሀይድ ይቆጠራሉ። ይህ የሀይድ አመጣጥ መጠይቅ (مسألة)  እንግዲህ ጎላ ብሎ የታወቀና ሸይኽ ዐብዱል አዚዝ ኢብኑ ባዝም ረሂመሁላህ የጠቀሱት ጉዳይ ነው።
    ሆኖም ሸይኽ ዐብዱል አዚዝ ኢብኑ ባዝ ራህመቱላሂ ዐለይሂ  ፈሳሾቹ ተከታትለው (ተያይዘው) መምጣታቸውን እንጂ ህመሙም አብሮ መገኘቱን መስፈርት አላደረጉም።
 በተጨማሪም የሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚንም የነበራቸው አባባልም ይኸው ነበር። ይህ ቢጫማና ቡናማ ፈሳሽ ከሀይድ ጋር እስካልተያያዘ ድረስ ሙሉ በሙሉ ከሀይድ አይቆጠርም የሚል ነው። ረሂመሁላህ

ሁለተኛው
            الصفرة والكدرة بعد الدم
                    وقبل الطهر
      ቢጫማ ወይም ቡናማ ፈሳሽ ከመንፃቷ በፊት ከሀይድ ፍሰት በኋላ መጨረሻ ላይ ከመጣ
   የሀይድ መቆም በግልፅ ከመታወቁ በፊት በሰተመጨረሻ ላይ ይህ ቢጫማ ወይም ቡናማ ፈሳሽ ከታያት ባለመቸኮል "ቀሰተል በይዳአ" የተሰኘው ነጭ ፈሳሽ እስኪመጣት መጠበቅ ይኖርባታል።
ለዚህ የሚረዳን አስረጅ
  ኢማሙ ማሊክ ረሂመሁላህ ዘግበውት
' ሙወጠእ ' በተሰኘው ድርሳናቸው ገፅ 130 ላይ እንደሰፈረውና ኡሙ ዐልቀመህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዳወራችን
{ ሴቶች ወደ የምእመናን እናት ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ፣ ቢጫማ የሀይድ ደም ያለበትን ጥጥ በ "ዱርጅ" ማለትም በእቃ ውስጥ አድርገው ይልኩባትና ሰላት መስገድ ይችሉ እንደሆን ይጠይቋት  ነበር። እሷም "ቀስሰተል በይዳአ" ማለትም ነጣ ያለ ፈሳሽ እስክታዩ ድረስ አትቻኮሉ ትላቸው ነበር። በአባባሏ የፈለገችውም ከሀይድ ፅዱ እስክትሆኑ ለማለት ነው። }
ሶስተኛው
           الصفرة والكدرة بعد الطهر
     ቢጫማ ወይም ቡናማ ፈሳሽ የወር አበባዋ አብቅቶ ከፀዳች  በኋላ የሚፈሳት ከሆነ
   ከሀይድ (ከወር አበባ) ፍሰት በኋላ የሚመጣ ቢጫማ ወይም ቡናማ ቀለም ያለው ፈሳሽ ከወር አበባ አይቆጠርም። ገላ ለመታጠብም የሚያስገድድ ስላልሆነ ዉዱእ በማድረግ ብቻ ሰላትንም ፆምንም መፈፀም ይቻላል።
ለዚህም አስረጃችን
   ኡሙ ዐጢየህ ረዲየላሁ ዐንሃ አንዳወራችን
« ከወር አበባ ከፀዳን በኋላ የሚመጣውን ቢጫማ ወይም ቡናማ ፈሳሽ ከምንም (ከወር አበባ) አንቆጥርም ነበረ ።»   
(ቡኻሪ ዘግበውታል)
የወር አበባ (ሀይድ) ከምን ያቅብሻል ? 🍁
       
✅ ሀይድን በተመለከተ የተለያዩ ነጥቦችን መዳሰስ በጀመርነው መሰረት በዛሬው መልዕክታችን ሀይድ ላይ ያለች እንስት ከምን መታቀብ እንደሚገባት እንመለከታለን።
✅ለሀይድ ወደ20 የሚደርሱ አህካሞች ይገኛሉ ከነዚያም መካከል በጣም አሳሳቢውንና ብዙሃን ሊያውቁትና ሊገነዘቡት የሚገባውን በማስቀደም እንጀምራለን።


No comments:

Post a Comment