Wednesday, 27 January 2016

PART 2 ልጆች

ልጆችን በጥሩ ተርቢያ ለማሳደግ ሁለት ጠቃሚ ምክሮች!

አባት ሆይ! በመጀመሪያ እናታቸውን ስትመርጥ መስፈርትህ መልካምና ዲን ያላት መሆኗ እንጂ ቆንጆ መሆንዋ አይሁን። ቁንጅናዋ ለልጆቿ ምንም አያሳስብም። ልጆች ቆነጆም ትሁን መልከጥፉ ለእናታቸው ቦታ ይሰጣሉ። ዲን ያላት ከሆነች ግን ይህ ለልጆቿ ክብር ነው።
ውድ ወላጆች! ለስኬታማ የልጆች አስተዳደግ ሁለት ወሳኝ እርምጃዎች ይጠበቁብናል፤
1) ለልጆች ጠንካራ ዱዓ ማድረግ ነው። ይህ የነብያት መንገድ ነው። ኢብራሂም አለይሂሰላም ያደረጉትን ዱዓ አስተውሉ፤

ﻭَﺇِﺫْ ﻗَﺎﻝَ ﺇِﺑْﺮَاﻫِﻴﻢُ ﺭَﺏِّ اﺟْﻌَﻞْ ﻫَٰﺬَا اﻟْﺒَﻠَﺪَ ﺁﻣِﻨًﺎ ﻭَاﺟْﻨُﺒْﻨِﻲ ﻭَﺑَﻨِﻲَّ ﺃَﻥ ﻧَّﻌْﺒُﺪَ اﻷَْﺻْﻨَﺎﻡَ

ኢብራሂምም ባለ ጊዜ (አስታውስ) «ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን፡፡» ኢብራሂም 35
በሌላም አንቀፅ እንደምናገኘው፤

ﺭَﺏِّ اﺟْﻌَﻠْﻨِﻲ ﻣُﻘِﻴﻢَ اﻟﺼَّﻼَﺓِ ﻭَﻣِﻦ ﺫُﺭِّﻳَّﺘِﻲ ۚ ﺭَﺑَّﻨَﺎ ﻭَﺗَﻘَﺒَّﻞْ ﺩُﻋَﺎءِ

«ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ» ኢብራሂም 40
2) ልጆችን በማቅረብና ከነሱ ጋር ብዙ ጊዜ በማሳለፍ ጥሩ አርአያ መሆን ያስፈልጋል። በጨዋታም ይሁን በቁምነገር እነሱን በመጎዳኘት ስነስርአትና መልካም ባህሪን ማስተማር፣ ተፅእኖም ማሳደር ይቻላል።
እነዚህ ሁለቱ የመልካም አስተዳደግ መሰረቶች ናቸው።
ልጆችን መግራት የሚቻለው በመምታት ወይም ክልከላዎችና ገደቦችን በመደርደር አይደለም። አትጫወት፣ አትናገር በማለት ልጆችን በምንፈልገው መልኩ መቅረፅ አይቻልም። እንደውም እልኸኛና ግትርነትን ያወርሳቸዋል።
አላህ ልጆቻችንን በመልካም ባህሪ ያንፅልን...አሚን!
ከሸይኽ ሙሀመድ ቢን አብድልወሀብ አልአቂል ምላሽ ተወስዶ ጥቂት ለውጥ የተደረገበት። 
---------------------------


No comments:

Post a Comment