አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ሴት ልጅ ልትረጋበት የሚገባ ተስማሚ ቦታ ቤቷ እንዲሆን አዟታል ፡፡ ይህን ሲናገር እንዲህ ይላል:-
وَقَرْنَ فِي بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ الْجَاهِلِيَّةِ الْأُولَى [٣٣:٣٣]
«በቤት ውስጥ እርጉ እንደመጀመሪያው መሃይነምነት ጊዜ መገላለጥን አትገላለጡ»
(አል አህዛብ ቁጥር 33)
እዚህ ላይ እንግዲህ አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ለሴት ልጅ በቤት ውስጥ መርጋትን አዟል ፡: ይህ ሲባል ግን በምንም አይነት ሁኔታ መንቀሳቀስ አትችልም ማለት ሳይሆን መሰረታዊ መርጊያዋና ስራዋ ቤት ውስጥ መሆን አለበት ፡፡
ይህ የሚጠቁመን ለአስፈላጊ ነገሮች መንቀሳቀስና መውጣት እንደምትችል ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ስለ ሃይማኖቷ ለማወቅ ፤ይህ እንደውም መሰረታዊ እውቀት (ፈርዱልዓይን) ከሆነና ባለችበት ቦታ ሊያስተምራት የሚችል አካል ከሌለ ግዴታ ይሆንባታል ፡፡
እንዲሁም ለሌሎች ጉዳይ ከሆነ ዘመናዊ እውቀት ለመገብየት፤ለስራና ለሌሎች ጉዳዮች ክልክላት(ሃራም)ን ርቃና የሌለበት እስከሆነ ድረስ አትከለከልም ፡፡
እዚህ ጋር ግን! በተለይ በተለይ ባለ ትዳር ከሆነች ባሏን መንከባከብና ልጆቿን በትክክለኛ እምነትና ስነምግባር ኮትኩታ ማሳደግ ግዴታ ይሆንባታል ፡፡ስለዚህ ከቤት መውጣት ለትምህርት ለስራና ለመሳሰሉት ጉዳዮች ከዚህ መሰረት ጋር የሚጋጭ ከሆነ ፍጹም አይፈቀድላትም፡፡
ኢስላም በውጭ ጥሮ ግሮ ማምጣትና ቤተሰቡን ማስተዳደር በወንድ ልጅ ላይ የጣለው ሃላፊነት ነው ፡፡ሴት ልጅ የፈለገ ንብረት አቅም ቢኖራትም ወዳና መርጣ ካላደረገች በስተቀር አትገደድም፡፡እንዲሁም ወልዳ ለምታጠባቸው ልጆቿ እራሱ ባሏን ቀጥሮ እንዲያስጠባ መጠየቅ ትችላለት ፡፡ሱብሃነላህ በጣም ይገርማል ከዚህ የበለጠ ልእልነትና ንግስትነት ምን አለ? አላህ ያሳውቀን፡፡
No comments:
Post a Comment