Wednesday, 27 January 2016

PART 1 የእንስቶች ወርሃዊው ዙር

🍁የእንስቶች ወርሃዊው ዙር🍁
አል ደውረቱ ሻህሪያ

ሙስሊሟ እንስት የሀይድ ማለትም የወር አበባ ጊዜዋ አብቅቶ ሰላት የምትጀምርበትን ቀን ለማወቅና የሌሎችንም ድንጋጌዎች አህካም ወይም ውሳኔ ለማወቅ እንዲረዳት የወር አበባዋን መጀመርያና ማብቂያ ማወቋ የግድ  ነው።
ይህ ቢያንስ ወደ ሃያ ከሚሆኑ የዲን ጉዳዮች ጋር የተቆራኘው የወር አበባ የደም ሂደት እንደ ግል ጉዳይ ብቻ ወይም እንደተራ ነገር የሚታይ ሳይሆን በያንዳንዱ ሙስሊም ቤተሰብና ማህበረሰብ ውስጥ ወሳኝ ሚና ያለው የሸሪዓ ክፍል ነው።
እንደሚታወቀውም ሴቶች በተለያዩ ምክንያቶች የተለያዩ የደም ዓይነቶች ይፈሷቸዋል።
ከነዚህም መሀከል
የሀይድ (የወር አበባ) ደም
የኢስቲሃዳ ደም 
(ከደም ስር የሚፈስ ደም ነው)
የኒፋስ (የወሊድ) ደም…
ዋናዎቹ ናቸው
~ ላሁኑ ትምህርታችን የምንመለከተው ሀይድ ስለሚባለው የደም ዓይነት ይሆናል።
ሀይድ ወይም የወር አበባ

👉 ስለ ሀይድ ደም ምን ያህል
ተገንዝበዋል ?
y የሀይድ ደም (የወር አበባ) በእንስቶች ላይ መኖር እነሱን የሚያነውራቸው አይደለም።
y የወር አበባ ደም ሴቷን ከወንዱ የሚለይ ቢሆንም ከወንዶች ዝቅ የሚያደርጋቸው ሰበብም አይደለም።
y አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንስቶችን ሲፈጥር ማህፀን እንዲኖራቸውና በዚያም ማህፀን ውስጥና በዙርያው አስፈላጊው የሆነውን የሆርሞን፣ የጅማት፣ የደምና የደምስርን እንዲሁም የተለያዩ አካላትን ፈጥሮለታል።
y ከዚህ ደምም ጋር ያለን ግንኙነት ከዚሁ ይጀምራል።
y በቦታው የሰው ልጅ ሰው ሆኖ ለመወለድ እስኪበቃ የሚያስፈልገውን ቀለብ ሁሉ ከዚያው ከማህፀን ውስጥ በዚሁ ደም አማካኝነት በእምብርት መስመር ነው ሲመገብ የሚያድገው።
y ከነዚያም መካከል ደም አንዱና በህይወት የመኖሩ ወሳኙ ነገር ነው።
📙የኢስላም ሊቃውንት (ዑለማእ) እንዳብራሩት:
የደሙ መንስኤ:
የሀይድ ደም ማለት ማህፀን የሚያመነጨውና ሴቷ ለአቅመ ሀዋእ ስትደርስ አብዛኛውን ግዜ በየወሩ የሚፈስሳት የደም አይነት ነው።
የቆይታ ግዜው:
የወር አበባ የታወቀ ወቅት አለው፤ በመሆኑም በአብዛኛውን ግዜ በአብዛኞች ላይ ለስድስትና ለሰባት ቀናት ወይም እንደሴቷ ተለምዶ ከዚህ ላነሰ ግዜና ለበለጠ ቀናትም ይቆይባቸዋል።
ቀለሙ:
የደሙ ቀለም ጠቆር ያለ ሲሆን ጥሩ ጠረንም የለውም።
ባህሪው:
ብዙሃኑ እንስቶች የወር አበባ ሲመጣባቸው እንደ ቁርጠት፣ የጀርባ ውጋትና የተለያዩ የሆድ ውስጥ ወይም ያጠቃላይ ሰውነት የመረበሽ ህመም ያስከትልባቸዋል።
በተለይ የመጀመርያቸው ሲሆን በጣም ይብስባቸዋል።
ከነዚህ አይነት ባህሪና ሁኔታ የተለየ ደም ከመጣባት ግን ሀይድ ሳይሆን የኢስቲሃዳ ደም ይሆናል።
y በእርግዝና ላይ የሌለች ሴትም እንደ ጤናማነቷ እና እንደ እድሜዋ በየወሩ ይህ የሀይድ ደም ይፈሳታል።
y ለፈጣሪ ጌታችን ለአላህ ምስጋና ይገባውና የወር አበባ ደምን በማህፀን ውስጥ እንዲሚመነጭ አድርጓል።
y እዚያ መቅረቱም አስፈላጊ ስላልሆነ በየወራቱ ለተወሰኑ ቀናት ወጥቶ እንዲፈስስ አደረገው።
ይህ የሰው ልጆች መፈጠርያ፣ ማደግያና የመጀመርያው የመኖርያ ስፍራችን ከዚህ ደም ጋር የቅርብ ጉድኝት ስላለው እንደማይመለከተን ሆነን ስለ ደሙ ከማወቅ ልንርቅ አይገባም።
y የወር አበባ ደም መፍሰሱ ጤናማነት እንጂ ጎጂ ጉዳይም አይደለም።

 ተፈጥሯዊነቱ

yየሀይድ (የወር አበባ) ደም ባብዛኛው እድሜያቸው ከ12 እስከ 50 ዓመታት ክልል ባሉትና አልፎ ኣልፎ ደግሞ ወደ 9 አመት እድሜ ወዳላቸውና እስከ 50 አመታት ባላቸው እንስቶች ላይ በየወሩ በታወቀ ግዜ የሚከሰትና ከማህፀን ወጥቶ የሚፈስሳቸው የተለመደና ጤናማ የሆነ የደም ዓይነት ነው።
yየሀይድ ጅምሩም ሆነ የማለቂያው የእድሜ ሁኔታ እንደ ሴቷ አስተዳደግ፣ ጤና፣ የአየር ሁኔታ ና ሌሎች ተፈጥሮዎች ስለሚለያይ ስለ አብዛኞች እንጂ ስለሁሉም መግለፅ ይከብዳል። እንዲሁም ተገድቦ የተነገረን ቁጥር ባለመኖሩ አንዲት እንስት የወር አበባነትን መስፈርት ያሟላ ደም ከታያት ስርኣቱንና ህግጋቱን መጠበቅ ግዴታ ይሆንባታል።
  ይህ ደም የመፍሰስ ባህሪ ስላለው ሀይድ ማለትም የሚጎርፍ ተባለ።
    ይህንንም ጥበበኛው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በሴቶች ላይ በዚህ መልኩ ደነገገ።
ኢማሙ ቡኻሪና ሙስሊም ረሂመሁሙላህ በዘገቡትና ከዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ በተነገረን መሰረትም የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስለ ሀይድ ደም ለራሷ ለዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ሲነግሯት:
« ይህ በኣደም ሴት ልጆች ላይ አላህ የፃፈው (የደነገገው) ነው። » ማለታቸው ተዘግቧል።
    ከሀይድ ባህሪም አንዱ ህመም ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽና የመሳሰሉት እንደየሴቷ ቢለያይም በየደረጃው ይከሰታል በመሆኑም በዚህ ሰበብ ለሚደርስባቸው ሁሉ ሰብር አድርገው የአላህን ጀልለ ጀላሉሁ ውሳኔና ጥበብ ሊወዱት ፣ ኣሚን ብለው ሊቀበሉት ግድ ይላቸዋል።

No comments:

Post a Comment