about-us

መግቢያ

   بسم الله الرحمن الرحيم

  ምስጋና ለዚያ ሁለቱን ተጣማሪ ወንድና ሴቶችን ለፈጠረ ፍቅርና ውዴታን በመሀከላቸው ላደረገው ጌታ ይሁን። ከርሱ ውጪ በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለ እመሰክራለው አንድና አጋር የሌለው ነው፡፡ ሙሀመድም የዕርሱ ባርያና መልዕክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለው የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው በቤተሰቦቻቸው በባልደረቦቻቸውና  እንዲሁም ፈለጋቸውን እስከ መጨረሻው በተከተሉ ሁሉ ላይ ይሁን።
   
    ይህ በተለያዩ ጊዜያት በተንቢሃት የፌስቡክና ዋትሳፕ ግሩፕ ፖስት ሲደረጉ የነበሩ ትምህርቶች ጥንቅር ነው፡፡ ዳሰሳ የሚያደርገውም አማኝ ሴቶችን በተመለከቱ የተለያዩ ኢስላማዊ ህግጋት ላይ ሲሆን ሙስሊሟ ሴት ኢስላም የሰጣትን ክብር ፀጋ እና ልዕቅና በተወሰነ መልኩም ቢሆን እንድትረዳና ኢስላማዊ ግዴታዎን እውቀትን መሰረት ባደረገ መልኩ ትወጣ ዘንድ አስተዋፅዖ ለማበርከት ነው። ሙስሊሟ ሴትም ለዱንያዋም ይሁን ለአኼራዋ የሚጠቅማትን ትምህርቶች ትቀስምበታለች ፤ ኢስላም ለሴቶች የሰጠውንም ታላቅ ደረጃ ትረዳበታለች ብለን አናምናለን። የሙስሊም እህቶችንም ህይወት በመልካም የሚለውጥ እንዲያደርገው አላህን እንማፀነዋለን።

No comments:

Post a Comment