ባለ ታሪኳ አንዲት ሂጃቧን በስርዓቱ ኒቃብ የምትለብስ እህት ነች ። ይህች እንስት በሃገረ ፈረንሳይ በአንድ ሱፐር ማርኬት ውስጥ የሚያስፈልጓትን እቃዎች እየገዛች ነበር።
እቃዋንም ገዝታ ከሰበሰበች በኋላ መክፈል ያለባትን ልትከፍል ወደ ሂሳብ ተቀባይዋ (ካሺየር) አመራች።
ሂሳብ መቀበያው ባንኮኒ ውስጥ የነበረችው እንስት የዘር ግንዷ ዓረብ የሆነች ለስሙ ለብሳለች ነገር ግን እርቃን የሆነች፣ የተራቆተች ሴት ነች።
ታዲያ ይህች እንስት ባለ ኒቃቧን በማፌዝ እይታ አየቻት። ማሾፏም ሳይበቃት እቃዋን እያነሳች ባንኮኒው ላይ እየወረወረች መቁጠር ተያያዘች።
ጥላቻዋን ለመግለፅ ነገር ፍለጋ መሆኑ ነው!… ነገር ግን ባለ ኒቃቧ እጅጉን የተረጋጋች ነበረችና በሁኔታዋ ምላሽ አልሰጠችም። ይህ መረጋጋቷ ግን ካሼሪዋን የበለጠ አናደዳት ቁጣዋን መቆጣጠር ሲያቅታትም እንዲህ አለች:-
« እኛ እዚህ ያለነው ሃይማኖት ወይም ታሪክ ለማቅረብ አይደለም። እምነትሽን መተግበር ወይም ኒቃብ መልበስ ካሰኘሽ ሃገርሽ ሂጂና እንደፈለግሽ ሁኚ።» አለቻት።
ባለ ኒቃቧ እቃዋን ወደ ቦርሳዋ ማስገባቱን ተወችና ዓረባዊቷን ካሼሪ ተመለከተቻት። አንድ ነገር ልታሳያትም ፈለገች...
ኒቃቧን ከፊቷ ላይ በማንሳት ፀጉረ ቡናማ፤ ዐይነ ሰማያዊ ፈረንሳዊት መሆኗን አሳየቻት። ከዚያም ለዚያች ከፈረንሳዮች በላይ ፈረንሳዊ ለሆነችው ካሼሪ እንዲህ አለቻት ፦
« ይህ እስላሜ ነው።❗ ይህ ደግሞ ሀገሬ ነው ። ! እናንተ እምነታችሁን ሸጣችኋል። እኛ ደግሞ ገዝተነዋል።»⚠ አለቻት።
ከዚህ አጭርና ቅፅበታዊ ታሪክ ኢስላም ድንበር የለሽና የማንንም ልቦና ካገኘ እንደሚያስውበው እንማርበት፡፡
በአንፃሩ እንደዚያች ዓረባዊት ክፉ ተፅዕኗቸው ግን እጅግ የበረታ መሆኑን ለመገንዘብ ያስችለናል።
No comments:
Post a Comment