በገላሽ ላይ ስላሉት ፀጉሮችና ስለ ጥፍሮችሽ በቂ መረጃ አለሽን ? 🌺 🌺 🌺
ለሸይኽ ሷሊህ አልዑሰይሚን ቀርበው ምላሽ ከተሰጡባቸው መስአላዎች [ረሂመሁላህ]
●ጥያቄ፡-
ሴት ልጅ ከመላው ሰውነቷ ፀጉሮችን ማስወገድ ይፈቀድላታልን ?
ይኸ ተግባር ለባል ከመቆነጃጀትስ ይቆጠራልን ?
ሴት ልጅ ከመላው ሰውነቷ ፀጉሮችን ማስወገድ ይፈቀድላታልን ?
ይኸ ተግባር ለባል ከመቆነጃጀትስ ይቆጠራልን ?
ምላሽ☞
« ለዚህ ጥያቄ የምንለው ምላሽ ሴት ልጅ ገላዋ ላይ ያለውን ፀጉር ማስወገድን በተመለከተ በሶስት እንደሚመደብ ነው።
① የመጀመርያው የተከለከለው አይነት ነው።
እሱም መቀንደብ [ነምስالنمص] ይባላል። እንዲያውም ይህንን አይነት ተግባር የፈፀመ ሰው የተረገመ ሆኗል።
ይህም ተግባር☞ ፊት ላይ የበቀለን ፀጉር መቀንደብ፣ መንጨት፣ መንቀል ነው። አደራረጉም የቅንድብ ፀጉሮችን [አልሐዋጂብالحواجب] በመንጨት ማሳሳትን፣ መቀነስን የመሰሉ ተግባራት ሲሆኑ የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] ቀንዳቢዋንና ተቀንዳቢዋን ረግመዋል።
② ሁለተኛው ፀጉርን የማስወገድ አይነት የተፈቀደው አይነት ነው።
ይህም ሊወገድ የሚገባውን እንደ የብብት ፀጉርና የብልት አካባቢ ፀጉርን ማስወገድ የሚለው ነው።
[ይኸ የታዘዝንበት ጉዳይ በመሆኑ ተፈላጊ ተግባር ነው።]
③ ሶስተኛው አይነት ደግሞ
ባቶች ላይ፣ ክንዶች ላይና ደረቶች ላይ እንዳሉትና የመሳሰሉት የፀጉር አይነቶች ሲሆኑ ይህንን ፀጉር በተመለከተ ዝም የተባለ፣ ስለሱ ምንም ያልተነገረለት አይነት ነው። በመሆኑም ይህን ዝም የተባለውን ሶስተኛውን የፀጉር አይነት ከማስወገድ ባለበት መተው የተሻለ ነው።
አላህ ይጠብቀንና አበቃቀሉ በርከት ያለ ሆኖ ሴቷ የሚያስጠላባት አይነት ከሆነ ብታሳሳው፣ ብትቀንሰው ችግር የለውም።
🔗 እንዲያውም ይህንን ፀጉር መቀነሷ፣ ማሳሳቷ ባሏ ዘንድ ይበልጥ የሚያስወድዳት ከሆነ ይህን ተግባር መፈፀሟ በጣም ጥሩና ቅድሚያ የሚሰጠው የሚበረታታ ይሆንላታል። ይህ ፀጉር ብዙ ካልሆነና የሚደብር ካልሆነ ግን ባለበት ሁኔታ መተዉ ይበልጥላታል።
ምክንያቱም አላህ ስለ ሸይጣን ሴራ ሲያስጠነቅቀንና ሸይጣን የተናገረውን ዛቻ ሲነግረን
﴿ولآمرنهم فليغيرن خلق الله﴾
[ النساء: 119 ]
«አዛቸውና የአላህን ፍጥረት ይለውጣሉ።» ያለው ቃል ውስጥ እንዳይከታት ያሰጋልና።
ነገር ግን የተጠላ [الكراهة] ወይም ሃራም የሆነ [التحريم] ተግባርነት ደረጃ አይደርስም። ማለትም ከእግር ባቶች፣ ከእጅ ክንዶች ሆነ ከደረት ላይ ያለውን ፀጉር ማስወገድ ወደ የተጠላ [الكراهة] ወይም ሃራም የሆነ [التحريم] ተግባርነት ደረጃ አይገባም። ምክንያቱም ይህን ተግባር የሚከለክል ማስረጃ አልመጣበትም። ሆኖም ዝም የተባለበት ጉዳይ ነውና ሴቷ ገላዋን አስጠሊታ እስካላደረገባት ድረስ ይህን ፀጉር ባለበት ሁኔታ ዝም ብትለው የተሻለ ነው።
በዚሁ አጋጣሚ ጥፍሮቻቸውን ባለበት በመተው በማሳደግ ረገድ ሸይጣን ስራዎቻቸውን ያጋጌጠባቸው አንዳንድ ሴቶችን የማስጠነቅቀው ጉዳይ አለኝ።
ይኸውም አንዳንድ እንስቶች [በተለይ] የአውራ ጣቶቻቸውን ጥፍር ያረዝሙታል። ይህ ደግሞ ተፈጥሮኣቸውን የሚፃረር ጉዳይ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት ይስፈንባቸውና ነቢዩ ለህዝባቸው የወሰኑትን የጥፍር መቆረጫ የመጨረሻውን የግዜ ገደብም ይቃረናል።
ነቢዩ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] ጥፍርን መቆረጥ፣ የብልት አካባቢ ፀጉርን ማስወገድ፣ የብብት ፀጉርን መንጨት በተጨማሪም ወንዶች ቀድሞ ቀመስ የሆነውን የላይኛው ከንፈር ፂማቸውን መቀነስ ከ40 ቀናት በላይ እንዳያልፋቸው ተናግረዋል።
የሚገርመው ግን የሰው ልጅ መጥፎ የሆነው ተግባሩ ጥሩ መስሎ አማምሮ ታየውና ይህ ቆሻሻ የሚሰበስብ፣ መጥፎ ሽታን የሚያጠራቅምና ሲያዩትም የሚያስጠላውን እንዲሁም ሀበሾች ጋር የሚያመሳስለውን ጥፍሩን የማሳደግ ተግባርን ይፈፅማል።
በቀድሞው ዘመን ከሀበሾች መካከል ጥፍሮቻቸውን በማርዘም እንደ ቢላዋ [አንድን ነገር ለመላጥ፣ ለመቁረጥ፣ ለመግፈፍ፣ ለመውጋት፣ ለመብሳትና ጥፍሮቻቸው የቻለውን በማድረግ ልክ ቢላን እንደ ሚጠቀሙት ሁሉ ይገለገሉበት] እንደ ስለት ይጠቀሙበት ነበር።
የአላህ ነቢይ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] እንዳሉትም
قال النبي عليه الصلاة والسلام: «ما أنهر الدم، وذكر اسم الله عليه فكل، إلا السن والظفر، فإن السن عظم، والظفر مدى الحبشة»،
«ከጥፍርና ከጥርስ ውጭ በሌላ ነገር ደሙ የፈሰሰን የአላህን ስም አውሳበትና ተመገበው። ምክንያቱም ጥርስ አጥንት ሲሆን ጥፍር ደግሞ የሀበሻ ቢላዋ ነውና።» ብለዋል።
በዚህም መሰረት አንድ ሰው ይህን ተግባር ሊፈፅም አይገባውም። ጥፍሩን፣ የብልቱን ፀጉር፣ የብብቱን ፀጉርና ወንዶች ደግሞ በተጨማሪነት የላይኛው ከንፈርን ፀጉር ከ40 ቀናት በላይ ማቆየትና ባለበት መተው የለበትም።»
🌴 🌴
በዚህም መሰረት አንድ ሰው ይህን ተግባር ሊፈፅም አይገባውም። ጥፍሩን፣ የብልቱን ፀጉር፣ የብብቱን ፀጉርና ወንዶች ደግሞ በተጨማሪነት የላይኛው ከንፈርን ፀጉር ከ40 ቀናት በላይ ማቆየትና ባለበት መተው የለበትም።»
🌴 🌴
📜ምንጭ፡-
ኑሩን አለድደርብ የካሴት ቁጥር [146]
ኑሩን አለድደርብ የካሴት ቁጥር [146]
No comments:
Post a Comment