Wednesday, 27 January 2016

PART 4 የእንስቶች ወርሃዊው ዙር

ሰላት
   የወር አበባ ላይ ላለች እንስት የፍላጎትንም ይሁን የግዴታ ሰላትን መስገዷ ይከለከላል።
👉 ከሀይድ በነፃችበት ወቅት የሰላቱ ወቅት አንድ ረከዓ የሚያሰግድ ያህል ካልቀራት በስተቀርም እንድትሰግድ አትገደድም።
   ይህም የሰላቱ ጅምር ወቅት ላይ ይሁን የመጨረሻው ወቅትም ላይ ቢሆን የደረሰችው ሙሉ አንድ ረከዓ የሚያሰግዳት ግዜ እያለ እሷ ንፁህ ከሆነች ቶሎ መስገድ አለባት።
   ምሳሌ:-
¹•  አንዲት እንስት መግሪብ ከገባ በኋላ ቢያንስ አንድ ረከዓ የሚያሰግድ ያህል ወቅት ከሄደ በኋላ ሀይድ ቢጀምራት ወደፊት ሀይዷን ካበቃችና ከፀዳች በኋላ ያንን የመግሪብ ሰላት ቀዷ ማውጣት ግድ ይሆንባታል፤ ምክንያቱም ንፁህ እያለች ወቅቱ ገብቷል ፤ እሷም ቢያንስ አንድ ረከዓ የመስገድ ዕድል ነበራት።
ለዚህም ምሳሌ:-
የመግሪብ ወቅት የሚጀምረው ከምሽቱ 12:00 ቢሆንና ሀይዷ የጀመራት 12:05 ቢሆን ወደፊት ከሀይድ ስትጠራ ያንን መግሪብ ሰግዳ ትተካለች።
👉  ነገር ግን መግሪብ እንደገባ በቅፅበት ወዲያው ሀይድ ቢጀምራት እዳ የመክፈል ግዴታ የለባትም።
²ከሀይዷ የነፃችው የሰላት ወቅቱ ማብቂያ ከሆነ
ምሳሌ:-
ፀሃይ ሳትወጣ አንድ ረከዓ ማሰገድ የሚያስችል ወቅት እያላት ከሀይዷ ከነፃችና ትንሽ ቆይቶም ፀሃይ ቢወጣ በመሰረቱ የፈጅር ወቅት አብቅቷል ነገር ግን ወቅቱ ሳያበቃ ስለነፃች ቀዷ ታወጣለች። ማለትም ፀሃይ ብቅ ብላ የፈጅር ወቅት የሚያበቃው ንጋት 12:00 ቢሆንና 11:55 ላይ ከሀይዷ ከነፃች እዳ አለባትና ከነጋም በኋላ ታጥባ ቀዷ ታወጣለች (ትሰግዳለች)።
👉 ነገር ግን ፀሃይ ልትወጣ ስትቀርብ በቅፅበት ወዲያው ከሀይዷ ከጠራች ቀዷ የለባትም።
ለሁቱም ምሳሌዎች አስረጅ የሚሆነን የአላህ መልዕክተኛ በነገሩን መሰረት ቡኻሪና ሙስሊም ረሂመሁሙላህ የዘገቡት ሀዲስ እነደዲህ ይላል:
من أدرك ركعة من الصلاة فقد أدرك الصلاة “   متفق عليه

« ከሰላት አንድን ረከዓ የደረሰ ሰላቱ ላይ ደርሷል »
  ማለትም ወቅቱ ሳያልፍ መጨረሻው ላይ አንድ ረከዓ የሚያሰግድ ወቅት አግኝቶ ሰላት የጀመረ ሰው … ምንም እንኳን ሰላቱን ሰግዶ ሲያበቃ የሰላቱ ወቅት ያለፈም ቢሆን እንኳ እንዳለፈበት አይቆጠርበትም።
   
    ዚክር እና ቁርኣንን መቅራት

   የወር አበባ ላይ ያለች እንስት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላን የምታወሳበትን ቃላቶች እንደ ተስቢህ፣ ታህሚድ፣ ተክቢርና ስትመገብ ቢስሚላህ ማለትን የመሳሰሉ እንዲሁም ሃዲስን ማንበብ፣ የፊቅህ ኪታቦችን ማንበብ፣ ዱዓእ ማድረግ፣ ዱዓእ ሲደረግ ኣሚን ማለት እና ቁርኣንን ማድመጥ በሙሉ ያለ ምንም ተቃውሞ ይፈቀድላታል። ክልከላ የለባትም።
   ቁርኣንነ ሲቀራ ማድመጥን በተመለከተም ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት መሰረት ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ሀይድ ላይ እያለች የአላህ መልዕክተኛ በደረቷ ላይ ተደግፈው ቁርኣን ይቀሩ ነበር እሷም ታደምጥ ነበር።
   በሌላ የኢማም ቡኻሪና ሙስሊም ዘገባም ኡሙ ዐጢያህ ረዲየላሁ ዐንሃ ከነቢዩ የሰማችውን እንደሚቀጥለው ገልፃለች:
« ለጋብቻ የደረሱም ልጃገረዶችም እንዲሁም ሀይድ ላይ ያሉ ሴቶችም ለሁለቱ ዒዶች ይወጣሉ። በዚህም መልካም ነገር ላይ ይሳተፋሉ፣ የምዕመናንን ዱዓእ ይቀበላሉ፤ ነገር ግን ሀይድ ላይ ያሉት ከሰላት ይርቃሉ። »
yቁርኣን መቅራትን በተመለከተ ሀይድ ላይ ያለች እንስት: በአንደበቷ ሳታነበንብ ፅሁፉን በዐይኗ መከታተሏና በልቧ ማስተዋሏ ምንም ችግር የለበትም።
 ኢማሙ ነወዊ ረሂመሁላህ 
" ሸርሁል ሙሀዘብ شرح المهزب " በተሰኘው ድርሳናቸው ላይ ባሰፈሩት መሰረት :
👉 ሀይድ ላይ ያለች እንስት በራሷ ቁርኣን ለመቅራት ከፈለገችና ፊትለፊቷ ተደርጎ ወይም ሰሌዳ ላይ ተፅፎ እያየች ከአንደበቷ ሳይወጣ በልቧ ብታነብ ያለ ምንም የምሁራን ኺላፍ የተፈቀደ ነው በማለት ገልፀዋል።
yቁርኣንን በአንደበቷ ማንበብን በተመለከተ አብዛኞቹ ሊቃውንት (ዑለማእ) ክልክል ነው አይፈቀድም ይላሉ።
ሀይድ ላይ ላለች ሴት ቁርኣንን ማንበቧ አይከለከልም የሚሉ መረጃዎች
¹ ኢማሙ ቡኻሪ፣ ኢብኑ ጀሪር አልጠበሪና ኢብኑ ሙንዚር ሀይድ ላይ ያለች ሴት ቁርኣንን በአንደበቷ ማንበቧ የተፈቀደ ነው ክልከላ የለበትም ብለዋል።
²  ከኢማሙ ማሊክና ሻፊዒይ ቀደም ካለው ንግግራቸው በተወራው መሰረትና ኢማሙ ቡኻሪይ " ፈትሁ ባሪ " ላይ  በኢብራሂም አልነኸዒ ንግግር ላይ አስተያየት ሰጥተው ባሰፈሩት መሰረትም  " ቁርኣን ማንበቡ ችግር የለውም " ብለዋል።
³ ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ በ " ፈታዋ " ድርሳናቸው ላይ እንደገለፁት:

በመሰረቱ ከቁርኣንም ይሁን ከሱና (ሀይድ ላይ ያለች እንስት እንዳትቀራ) የሚከለክላት መረጃ የለም ብለዋል።" ሀይድ ላይ ያለች ሴትም ትሁን ጀናባ የሆነ ሰው ቁርኣን ምንም አያነብም። " የተባለው ሀዲስ የዘርፉ ማለትም የሀዲስ ሊቃውንት በሆኑት ስምምነት መሰረት ደዒፍ ነው።በነቢዩ    ዘመን ሴቶች ሀይድ ይፈሳቸው ነበር፤ ቁርኣንን መቅራቷ እነደ ሰላት ሁሉ ክልክል ቢሆንባት ኖሮ ነቢዩ  ለህዝባቸው ከሚያስጠነቅቁት ጉዳይ ኣንዱ ይሆን ነበር። የምእመናን እናቶችንም ያስተምሩ ነበር። ይህንንም ጉዳይ እነሱ ለተቀሪው ሰው ከሚያስተላልፉት መረጃ ይካተት ነበር።
 በመሆኑም ከመልእክተኛው  ኣንድም ሰው ሀይድ ላይ ያለች ሴት ቁርኣንን እንዳታነብ የሚል መረጃ ካላስተላለፈ ይህ ነገር ክልክል ማለት አይፈቀድም።
   እንደሚታወቀው እሳቸው ያንን ጉዳይ አልከለከሉምና።
   በዘመናቸው በርካታ እንስቶች ሀይድ አየመጣቸው እየታወቀም ቁርኣንን አታንብቡ ብለው አልከለከሉም።
ስለዚህም ሃራም ኣለመሆኑ ታወቀ ማለት ነው። )
"   የሸይኩል ኢስላም ንግግር አብቅቷል። "
* የምሁራንን አስተያየትና ልዩነት ከተረዳን ፤ ከኛ የሚጠበቀው
👉 የኢስላም ሊቃውንት እንዳስረዱት አስፈላጊ ጉዳይ ካልገጠማት በስተቀር ሀይድ ላይ ያለች እንስት ቁርኣንን በአንደበቷ ባታነብ የተሻለ ነው።
ለምሳሌ:
y የቁርኣን አስተማሪ ከሆነችና ተማሪዎቿን ማረም ካስፈለጋት ብታነብ ወቀሳ የለባትም።

yእንዲሁም የቁርኣን ተማሪ ከሆነችና ሀይዷ የመጣባትም በዚሁ በፈተና ወቅቷ ከሆነ ለፈተናው ስትልና ለመሳሰሉት አስፈላጊ ጉዳዮች ብታነብ አግባቢ እንደሆነ ሊቃውንት ያስረዳሉ  ።

No comments:

Post a Comment