Wednesday, 27 January 2016

ለባለቤትሽ ተዋቢ

የሚያሳዝነው ብዙ ሴቶች መዋብን እና መጋጌጥን ከቤት ውጪ ለሆነ ጉዳይ ወይም ስብሰባ ለመውጣት በፈለጉ ግዜ እንጂ አያውቁትም፤ የባልን ሐቅ በተመለከተ ግን ፡ ወደ ቤት በገባ ግዜ በተጎሳቆለ ልብስ፣ጥሩ ባልሆነ ሽታ፣ በተነጨባረረ ፀጉር ፣ እንዲሁም እሱ ወደሷ ያለውን ፍላጎት የሚገቱ ገፅታዎችን ተላብሳ ትቀበለዋለች።
ታድያ እንደዚህ አይነት ገፅታን ወደ ተላበሰች (ሚስት) ምን አይነት ፍላጎት የዚህን ባል ቀልብ ሊሞላ ይችላል?
ከእርሱ ጋር ሁኔታዋ እንዲህ ከሆነ፣ ምን አይነት ፍቅርስ ልቡን ከቦ ሊይዘው ይችላል?
ይሄ የሴቶችን ሞኝነት እና የትዳራቸውን ህይወት ለሟሟላት  እንዲሁም (ትዳር ውስጥ) ያላቸውን  ደረጃም ለመጠበቅ ፤ ያላቸውን የአስተሳሰብ ጉድለት የሚያመላክት ነው።
የመልካም ሚስት  ባህሪ  ከሚለው  የሸይኽ ዐብድ ረዛቅ  አልበድር ሀፊዘሁላህ ኪታብ  ከገፅ 24 የተወሰደ
።።።።።።።።።።።።።።።።
ዋነው ትዳር  መያዙ  ብቻ  በቂ  አይደለምና  ሀቁንም ተወጪ፡፡
እህቴ   ንፅህናሽን  ጠብቂ አምረሽ  ተውበሽ ጠብቂው  !  በተገላቢጦሽ  ከሆንሽ  ግን  እንደሚንቅሽ  በእሱ ዘንድ  ያለሽ  ክብረም  እንደሚቀንስ እወቂ፡፡  በልቡ ውስጥ  ላንቺ  ያለው  ፍቅር  መንምኖ እንድያልቅ ምክንያት አትሁኚ! በመሀከላችሁ ደግሞ ፍቅር  ከሌለ  አስቢው  ቀሪው  ሂወትሽ  ምን  እንደሚሆን?
" ሴት  ልጅ  እንደ  ብርጭቆ ነች  አንዴ  ከተሰበረች  መጠገን  አንችልም"  እና  ልብ  በይ
ውዷእህቴ የባልሽን  ሀቅ  አደራ!
አላህ  የመልካም  ሚስት  ባህሪን  ያላብሰን  የባል  ሀቅ  ጠባቂ  ያድርገን


No comments:

Post a Comment