የቂያማ ምልክቶች
የቂያማ ምልክቶች ሲባል ቂያማ ከመምጣቱ በፊት መቃረቡን የሚጠቁሙ
ክስተቶች ማለት ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
{
فَهَلْ يَنْظُرُونَ إِلَّا السَّاعَةَ أَنْ تَأْتِيَهُمْ بَغْتَةً فَقَدْ جَاءَ
أَشْرَاطُهَا } (محمد : 18)
‹‹ሰዓቲቱንም ድንገት የምትመጣባቸው መኾንዋን እንጅ ይጠባበቃሉን? ምልክቶችዋም በእርግጥ መጥተዋል፡፡››
ሙሐመድ 18
የቂያማ ምልክት አይነቶች
የቂያማ ምልክቶች በሶስት ይከፈላሉ
አንደኛው፡- ራቅ ያሉ ምልክቶችና ተፈፅመው ያበቁ ናቸው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ከሚካተቱ ምልክቶች አንዱ
የነብዩ صلى الله عليه وسلم መላክ ነው፡፡ አነስ ኢብን ማሊክ በአስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ صلى
الله عليه وسلم የመሀልና የአመልካች ጣታቸውን
በማያያዝ እኔና ቂያማ እንዲህ ተቀራርበን መጣን፡፡” ብለዋል
ከዚህ ክፍል ውስጥ የጨረቃ መሰንጠቅ ይጠቀሳል፡፡ አላህ እንዲህ
ይላል
{
اقْتَرَبَتِ السَّاعَةُ وَانْشَقَّ الْقَمَرُ } (القمر : 1)
‹‹ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፡፡››
አል ቀመር 1
ሂጃዝ ውስጥ የተቀሰቀሰ እሳት ነበልባል ቡስራ ድረስ መታየቱ፡፡
ቡኻሪና ሙስሊም ከአቡ ሑረይራ በአስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ صلى
الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል
«
لا تقوم الساعة حتى تخرج نار من أرض الحجاز تضيء أعناق الإبل ببصرى »
“ቂያማ ከመቆሙ በፊት ሂጃዝ ላይ እሳት ተነስቶ ቡስራ ያሉ ግመሎች
አንገት ላይ የነበልባሉ ነፀብራቅ ይታያል፡፡” (ቡኻሪ 7118 ሙስሊም 29ዐ2)
ነብዩ صلى الله عليه
وسلم ባሉት መሰረት ይህ እሳት በጁማደል አኺር ወር በስድስት መቶ ሃምሳ አራተኛ የሒጅራ አመት በመዲና በስተምስራቅ
አካባቢ ተነስቶ ከፍተኛ ንዳድ የተፈጠረ ሲሆን የሻም ህዝቦች የእሳቱን ብርሃን እንደተመለከተ እንዲሁም የቡስራ ህዝብ በእሳቱ ብርሃን
የግመሎችን አንገት እንዳዩ ታሪክ ዘግቧል፡፡
ሁለተኛው፡-
መካከለኛ የቂያማ ምልክቶች ሲሆን
የተከሰተ ወደፊት የሚከተቱ ምልክቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ ለምሳሌ፡-
የሴት ባሪያ ጌታዋን መውለድና የታረዙ ድሆች በፈጣን ጊዜ ውስጥ
ለግንባታ መፎካከር፡፡ ሙስሊም በዘገቡት የጅብሪል ሀዲስ እንደተዘገው
«
قال فأخبرني عن الساعة ؟ قال : ما المسئول عنها بأعلم من السائل . قال : فأخبرني
عن أماراتها ، قال : أن تلد الأمة ربتها ، وأن ترى الحفاة العراة العالة رعاء
الشاء يتطاولون في البنيان »صحيح مسلم برقم (8)
“ጅብሪል ለነብዩ صلى الله عليه وسلم ቂያማ እለት መች እንደሚሆን ንገርኝ ሲላቸው ተጠያቂ ከጠያቂ ይበልጥ ስለዚህ አያውቅም አሉት በማስከተል
እንግዲያውስ ስለ ምልክቶቿ ንግሩኝ ሲላቸው እንዲህ ሲሉ ነገሩት ሴት ባሪያ ጌታዋን መውለድ፣ ጫማ ያልነበረው የታረዘ ድሃ እረኛ የነበሩ ለግንባታ መሽቀዳደም፡፡” (ሙስሊም 8)
ነቢይ ነኝ የሚሉ ሰላሳ ውሸታሞች መምጣት፡፡
አቡሑረይራ በአስተላለፉት ሀዲስ
ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል
«
لا تقوم الساعة حتى يبعث دجالون كذابون قريبا من ثلاثين كلهم يزعم أنه رسول الله » رواه البخاري برقم (3609)
“ቂያማ ከመከሰቱ በፊት ወደሰላሳ የሚሆኑ ውሸታሞች ነቢይ ነኝ በማለት
ብቅ ይላሉ፡፡” (ቡኻሪ 36ዐ9)
ሶስተኛው፡- ታላላቅ ምልክቶች
እነዚህ ምልክቶች መከሰታቸውን
ተከትሎ ቂያማ ይቆማል
እነዚህ ምልክቶች አስር ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ አንዱም አልተከሰተም፡፡
ኢማም ሙሰሊም ከሁዘይፋ ኢብን አስየድ እንዳስተላለፉት
«
اطلع النبي صلى الله عليه وسلم علينا ونحن نتذاكر ، فقال : ما تذاكرون ؟ قالوا :
نذكر الساعة . قال : إنها لن تقوم حتى تروا قبلها عشر آيات : فذكر الدخان والدجال
، والدابة ، وطلوع الشمس من مغربها ، ونزول عيسى ابن مريم صلى الله عليه وسلم ،
ويأجوج ومأجوج ، وثلاثة خسوف : خسف بالمشرق وخسف بالمغرب وخسف بجزيرة العرب ، وآخر
ذلك نار تخرج من اليمن تطرد الناس إلى محشرهم » صحيح
مسلم
“በሆነ እለት አብረን እየተዋወስን ሳለን ነቢዩ صلى الله عليه وسلم ወደኛ ብቅ አለሉና “ምንድ ነው ምትመካከሩት?” አሉን እኛም “ቂያማን እየተዋወስን ነው” ብለን መለስን
እሳቸውም እንዲህ አሉ “አስር ተአምሮች ሳይከሰቱ ቂያማ አይቆምም ከዚያ አስሩን ሲዘረዝሩ ጭስ፣ ደጀል፣ እንስሳ፣ የፀሐይ ከምዕራብ
መውጣት፣ የኢሳን መውረድ፣ የእጁጅና መእጁጅ ፣ ሶስት የመሬት መስመጦች በምስራቅ በኩል የሚከሰት መስመጥ በምዕራብ በኩል የሚከሰት
መስመጥና የአረብ ደሴት በኩል የሚከሰት መስመጥን ጠቅሰው የመጨረሻው
ከየመን ተቁስቅሶ ሰዎችን ወደ መሰብሰቢያቸው የምትሰድ እሳት እንደምትቀሰቀስ ተናገሩ፡፡” (ሙስሊም 2901)
በሌሎች ሀዲሶች የመህዲ መምጣት የከዕባ መፍረስና የቁርአን ከምድር መነሳት ተነግሯል፡፡ አብዛኞች
ዑለማዎች እንደሚሉት ከሆነ አስሩ የቂያማ ምልክቶች ከላይ የተጠቀሱ ሶስቱ ምልክቶችና የሁዘይፋ ኢብን አስየድ ሀዲስ ላይ ከተጠቀሱት
ከመሬት መስመጥ ውጭ ያሉ ምልክቶች ናቸው፡፡ የመሬት መስመጥ ሀዲሱ ላይ እንደተባለ ከቂያማ ምልክቶች አንዱ ቢሆንም ከአስሩ ምልክቶች
ቀደም ብሎ የሚከሰት ምልክት ነው፡፡
No comments:
Post a Comment