በቁርአን ማመንና መለያዎቹ
ቁርአን የአላህ ንግግር ሲሆን ቃሉም ትርጉሙም ከአላህ
የመነጨና ጂብሪል ከአላህ በመስማት ወደ ነቢዩ ﷺ ያስተላለፈው ከብረዛና ከመዛባት የተጠበቀ መፅሐፍ
ነው፡፡
የቁርአን መለያዎች
በአላህ መፃህፍት ማመን ከኢማን ማፅዘናት አንዱ ነው፡፡
ይሁንና ቁርአን ሌሎችን መፃህፍት የሚሰርዝ የሁሉም የበላይ ፈራጅና ነቢዩ ﷺ
ከተላኩ በኃላ የሁሉም ሰውና ጋኔን መመሪያ በመሆኑ ከአላህ ዘንድ በወረዱና ከመበረዛቸው በፊት ባሉበት ሁኔታ በሁሉም መፃህፍት
ማመን እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ ቁርአንን ከሌሎች የምንለይባቸው እምነቶች አሉ፡፡ ከነዚህ መለያዎቹ የቁርአን ጥሪና ህግጋቶቹ ሁሉንም ሰውና ጋኔን የሚያካትትና
ማንም ቢሆን ቁርአንን መመሪያ ሳያደርግ አላህን በሌላ ህግጋት ማምለክ እንደማይፈቀድለት ማመን፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
{ تَبَارَكَ الَّذِي نَزَّلَ الْفُرْقَانَ عَلَى عَبْدِهِ
لِيَكُونَ لِلْعَالَمِينَ نَذِيرًا } (الفرقان : 1)
‹‹ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው፡፡›› ፉርቃን 1
በሌላም የቁርኣን አያት ለነብያችን ﷺ
እንዲህ እንዲሉ አዟቸዋል፡-
{ وَأُوحِيَ إِلَيَّ هَذَا الْقُرْآنُ لِأُنْذِرَكُمْ بِهِ وَمَنْ
بَلَغَ } (الأنعام : 19)
‹‹ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውን ሰው ሁሉ በርሱ ላስጠነቅቅበት ወደኔ ተወረደ (በላቸው)›› አል አንዓም 19
ስለጋኔኖችም ሲናገር እንዲህ ይላል
{ إِنَّا سَمِعْنَا قُرْآنًا عَجَبًا }{ يَهْدِي إِلَى الرُّشْدِ
فَآمَنَّا بِهِ } (الجن : 1 ، 2)
‹እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርኣን ሰማንም፤ ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን (ቁርአን ሰማን)፡፡ በእርሱም አመንን፡፡ ›› አል ጂን 1-2
ከፊቱ የነበሩትን መፃህፍት የሰረዘ መሆኑን ማመን፡፡
የመፅሐፍ ባለቤቶችም ሆኑ ሌሎች ቁርአን ከወረደ በኃላ በሌላ መመሪያ አላህን ማምለክ እንደማይችሉ፣ ቁርአን ሀላል ያደረገው
እንጂ ሀላል እንደሌለ ቁርአን ሀራም ካደረገው ውጭ ሀራም እንደሌለ ማመን፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል
{ وَمَنْ يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَنْ يُقْبَلَ
مِنْهُ } (آل عمران : 85)
‹‹ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም›› አል ዒምራን 85
{ إِنَّا أَنْزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ
بِالْحَقِّ لِتَحْكُمَ بَيْنَ النَّاسِ بِمَا أَرَاكَ اللَّهُ } (النساء : 105)
‹‹እኛ በሰዎች መካከል አላህ ባሳወቀህ ልትፈርድ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት አወረድን፡፡›› አል ኒሳእ 1ዐ5
ቀደም
ብሎ በተጠቀሰውም የአህሉል ኪታቦችን መፅሐፍ ማንበብ በሚከለክለው የጃቢር ሀዲሰ ነብዩ ﷺ
እንዲህ ብለዋል
( . . . « والذي نفسي بيده لو أن موسى كان حيًّا ما وسعه إلا أن
يتبعني » واه الإمام أحمد في المسند : 3 / 387 ،
وغيره
“ነፍሴ በእጁ ባለው ጌታ እምላለሁ ሙሳ እንኳን ህያው ቢሆን እኔን ከመከተል ውጭ አማራጭ የለውም፡፡” (ሙስነድ አህመድ 3/387)
“ነፍሴ በእጁ ባለው ጌታ እምላለሁ ሙሳ እንኳን ህያው ቢሆን
እኔን ከመከተል ውጭ አማራጭ የለውም፡፡”
ቁርአን ያመጣው ህግጋት ከሌሎች መፅሐፍት በተቃራኒ ገርና
ቀላል ነው፡፡ በአንፃሩ የቀድሞ መፅሐፎች ብዙ ከባድ ሸክም ነበረባቸው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል
{ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الرَّسُولَ النَّبِيَّ الْأُمِّيَّ
الَّذِي يَجِدُونَهُ مَكْتُوبًا عِنْدَهُمْ فِي التَّوْرَاةِ وَالْإِنْجِيلِ
يَأْمُرُهُمْ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَاهُمْ عَنِ الْمُنْكَرِ وَيُحِلُّ لَهُمُ
الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ وَيَضَعُ عَنْهُمْ إِصْرَهُمْ
وَالْأَغْلَالَ الَّتِي كَانَتْ عَلَيْهِمْ } (الأعراف : 157)
‹‹ለእነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ የኾነውን መልክተኛ
የሚከተሉ ለኾኑት (በእርግጥ እጽፍለታለሁ)፡፡ በበጎ ሥራ ያዛቸዋል፡፡ ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል፡፡ መልካም ነገሮችንም
ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፡፡ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል፡፡ ከእነሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም
በእነርሱ ላይ የነበሩትን እንዛዝላዎች (ከባድ ሕግጋቶች) ያነሳላቸዋል፡፡›› አል አዕራፍ 157
ቁርአን አላህ ለመጠበቅ ኃላፊነት የወሰደለት ብቸኛው
መፅሐፍ ሲሆን ይህ ጥበቃ ቃሉንም ትርጉሙንም የሚያካትት ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል
{ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ
} (الحجر : 9)
‹‹እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡›› ሂጅር 9
{ لَا يَأْتِيهِ الْبَاطِلُ مِنْ بَيْنِ
يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِ تَنْزِيلٌ مِنْ
حَكِيمٍ حَمِيدٍ } ( فصلت : 42)
‹‹ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ው፡፡›› ፉሲለት 42
{ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ }{
فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ }{ ثُمَّ إِنَّ عَلَيْنَا بَيَانَهُ }
(القيامة : 17-19)
‹‹(በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡ ባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል፡፡ ከዚያም
ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው፡፡ ›› አል ቂያማህ 17-19
በመጨረሻው አንቀፅ ትርጉም ዙሪያ ኢብን ከሲር
እንዲህ ይላሉ
“ቁርአን ከተነበበና ከተሸመደደ በኃላ እናብራራልሃለን
ትርጉሙንም በምንፈልገው መልኩ እናሳውቅሃለን፡፡”
አላህ ከነቢዩ ﷺ
ጀምሮ እስካሁን ድረስ ቁርአንን በመሸምደድ፣ በመጠበቅ፣ ትርጉሙን በመረዳትና በቁርአን በመስራት ኃላፊነትን በሚገባ የሚወጡ
ምሁራንን አመቻችቷል፡፡ እነዚህ ዑለማዎች ቁርአንን ለመንከባከብ የሚያስችሉ መድረኮችን ሁሉ በመጠቀም በቁርአን የተለያዩ ርዕሶች
ዙሪያ የተለያዩ መፅሐፎችን ደርሰዋል፡፡ አንዳንዱ በትርጉሙ ዙሪያ ሌላው በንባቡ ዙሪያ፣ ስለሙህከምና ሙተሻቢህ፣ መካና መዲና
ስለወረዱ ምዕራፎች፣ ስለህግጋቶቹ፣ ስለስራዥና ተሰራዡ፣ አንቀፆቹ ስለወረዱባቸው ምክንያቶች፣ ስለቁርአን ምሳሌዎች፣ ስለቁርአን
ተአምራት፣ ስለቃላት ትርጉሞች፣ ስለ ሰዋሰውና ሌሎችም የቁርአን ትምህርቶች በተለያየ መልኩ በመፃፍ አላህ በነዚህ ዑለማዎች ምክንያት
ቁርአን የተጠበቀ ሆኖ እንዲቆይ አድርጓል፡፡
ቁርአን በማንኛውም ፍጡር አምሳያ ሊመጣ የማይቻል በአገላለፅ
ብቃቱ ጣሪያ የነካ በመሆኑ ሰዎችና ጋኔን በአጠቃላይ የቁርአንን አምሳያ ወይም ከፊሉን ከቻሉ እንዲያመጡ በሶስት ደረጃ
ሞከራቸው፡፡
በመጀመሪያ
{ أَمْ يَقُولُونَ تَقَوَّلَهُ بَلْ لَا يُؤْمِنُونَ }{
فَلْيَأْتُوا بِحَدِيثٍ مِثْلِهِ إِنْ كَانُوا صَادِقِينَ } (الطور : 33 ، 34)
ወይም «ቀጠፈው ይላሉን?» አይደለም፤ በእውነቱ አያምኑም፡፡ እውነተኞችም ቢኾኑ መሰሉ
የኾነን ንግግር ያምጡ፡፡›› ጡር 33-34
በፍፁም የማይችሉት ነገር መሆኑን ደግሞ እንዲህ
በማለት አፀና፡፡
{ قُلْ لَئِنِ اجْتَمَعَتِ الْإِنْسُ وَالْجِنُّ عَلَى أَنْ
يَأْتُوا بِمِثْلِ هَذَا الْقُرْآنِ لَا يَأْتُونَ بِمِثْلِهِ وَلَوْ كَانَ
بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ ظَهِيرًا } (الإسراء : 88)
«ሰዎችም ጋኔኖችም የዚህን ቁርኣን ብጤ በማምጣት ላይ ቢሰበሰቡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳት ቢሆንም እንኳ ብጤውን አያመጡም» በላቸው፡፡ ››(አል ኢስራእ 88)
No comments:
Post a Comment