ህዝቦች ላይ ግዴታ የሆኑ የነቢዩ صلى
الله عليه وسلم መብቶች
5 እሳቸው ላይ አብዝቶ ሰላትና ሰላም ማውረድ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
{إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ
عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا
تَسْلِيمًا } (الأحزاب : 56)
‹‹አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ እናንተ
ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ የማክበርንም ሰላምታና ሰላም በሉ››
አል አህዛብ 56
አብደላህ ኢብን አምር ኢብኑል ዓስ በአስተላለፉት ሀዲስ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል
«
من صلى علي صلاة صلى الله عليه بها عشرا »
“እኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰላት ያወረደ አላህ እሱ ላይ አስር ጊዜ ያወርዳል፡፡” (ሙስሊም 384)
ዓሊይም በአስተላለፉት ሀዲስ ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ
ይላሉ
«
البخيل الذي من ذكرت عنده فلم يصل علي »
“ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ ስሜ ተነስቶ ሰላት የማያወርድብኝ ነው፡፡”
(ቲርሚዚይ 3546)
ሰላትና ሰላም በሁሉም ነቢያት ላይ ተገቢ ቢሆንም ነገር ግን ነቢያችን صلى
الله عليه وسلم ላይ ይበልጥ ተፈላጊ ነው፡፡
እንዲያውም አንዳንድ ዑለማዎች እንዳሉት እሳቸው ላይ ሰላትና ሰላም ማውረድ ዑለማዎች የሚስማሙበት ግዴታ ነው፡፡
ቃዲ ኢያድ እንዲህ
ይላል “ነቢዩ صلى الله عليه وسلم ላይ ሰላት ማውረድ ጊዜ ሳይወሰን በጥቅሉ ግዴታ ነው፡፡
ምክንያቱም አላህ ያዘዘው ተግባር በመሆኑና የዑለማዎችም የተስማሙበት ጉዳይ ስለሆነ፡፡”
6 ለነቢዩ صلى
الله عليه وسلم ተገቢ በሆኑ ደረጃዎችና
መለያዎችን ማመን፡፡ ከላይ የተጠቀሱ የነቢዩን صلى الله عليه
وسلم የላቁ ማዕረጐችን ማመን
ማወደስ፣ ለሰዎች ማሰራጨትሃ ለህፃናትም ማስተማር፡፡
7
ነቢዩ صلى الله عليه وسلم ላይ ድንበር ከማለፍ መጠንቀቅ፡፡ አላህ ለነቢዩ صلى الله عليه وسلم ህዝቦችን እንዲህ እንዳሉ ያዛል፡፡
{ قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِثْلُكُمْ يُوحَى إِلَيَّ
أَنَّمَا إِلَهُكُمْ إِلَهٌ وَاحِدٌ فَمَنْ كَانَ يَرْجُوا لِقَاءَ رَبِّهِ
فَلْيَعْمَلْ عَمَلًا صَالِحًا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا }
(الكهف : 110)
«እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡
የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ»
በላቸው፡፡ (አል ከህፍ 11ዐ)
{ قُلْ لَا أَقُولُ لَكُمْ عِنْدِي خَزَائِنُ اللَّهِ وَلَا
أَعْلَمُ الْغَيْبَ وَلَا أَقُولُ لَكُمْ إِنِّي مَلَكٌ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا
يُوحَى إِلَيَّ } (الأنعام : 50)
«ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም አላውቅም፡፡ ለእናንተም
እኔ መልአክ ነኝ አልልም፡፡ ወደእኔ የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም»
በላቸው፡፡ (አል አንዓም
5ዐ)
በዚህ አንቀፅ አላህ ነቢዩ ነቢይነታቸውን ብቻ እንዲያፀድቁና ከአላህ
ጌትነትና ስልጣን የጋራ እንዳልሆኑ ግልፅ እንዲያደርጉ ያዛል፡፡
ነቢዩም صلى
الله عليه وسلم እሳቸውን በማወደስና በማሞካሸት
ድንበር እንዳይታለፍባቸው አስጠንቅቀዋል፡፡
ኢማም አል ቡኻሪ ከኡመር ኢብኑል ኸጣብ እንዳስተላለፉት ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል
« لا تطروني
كما أطرت النصارى ابن مريم فإنما أنا عبده ، فقولوا : عبد الله ورسوله »
“ክርስቲያኖች የመርየምን ልጅ ኢሳን በማወደስ ድንበር አንዳለፉበት
እኔንም በማሞካሸት ወሰን አትለፉ፡፡” (ቡኻሪ 3445)
ኢብኑ አባስ እንዳሉት “አንድ ሰው ወደ ነቢዩ صلى
الله عليه وسلم ጋር በመምጣት በአንድ ጉዳይ
ካወራቸው በኃላ አላህና እርሶ የፈለጉት ሆነ ሲላቸው እሳቸውም
“የአላህ ቢጤ አደረከኝ አንዴ አላህ ብቻ የፈለገው ሆነ በል አሉት፡፡” (ሙስነድ አህመድ 1/214)
ነቢዩ
صلى الله عليه وسلم ከሚገባቸው ደረጃ በማሳለፍ እሳቸው ላይ ድንበር እንዳይታለፍ በመከልከላቸው በየትኛውምም የወሰን ማለፍ አይነት
እሳቸው ላይ ድንበር ማለፍ የተከለከለ ነው፡፡ ነቢዩ صلى
الله عليه وسلم ላይ ወሰን ከማለፍ አይነቶች
ለምሳሌ “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ እንዲህ አድርጉልኝ ፣ ይህን ፈፅሙልኝ በማለት ለመለመን ክልክል ነው፡፡ ይህ ድርጉት ድዓዕ በመሆኑ
ዱዓን ዱዓን ከአላህ ውጭ ማድረግ አይፈቀድም፡፡ እንዲሁም ለነቢዩ
صلى الله عليه وسلم ማረድ ስለት ማቅረብ፣ በቀብራቸው ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ ወይም ወደ ቀብራቸው ዞሮ መስገድ እነዚህ ሁሉ ክልክል
የሆኑ የድንበር ማለፍ አይነቶች ናቸው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
{ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي
لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ }{ لَا شَرِيكَ لَهُ وَبِذَلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا أَوَّلُ
الْمُسْلِمِينَ }
(الأنعام : 162 ، 163)
«ስግደቴ፣ መገዛቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው»
በል፡፡ «ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም (በማጥራት) ታዘዝኩ፡፡ እኔም
የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» (በል)፡፡
(አል አንዓም 162-163)
8 ከነብዩ صلى
الله عليه وسلم መብቶች ውስጥ የርሳቸውን
ሰሃቦች ቤተሰቦቻቸውንና ባለቤቶቻቸውን ማክበር አንዱ ነው፡፡ አላህ ሶሃባችን እንድናከብርና ምህረትንም እንድለምንላቸው ስላዘዘ እነሱን
ከመጥላትና እነሱ ላይ ነውርን ከመፈለግ መጠንቀቅ ግድ ነው፡፡
አላህ ሙሃጂሮችንና አንሳሮችን ከጠቀሰ በኃላ ከነሱ ቀጥሎ የሚመጣ ትውልድ ለነሱ ምህረትን እንዲጠይቅና ልቡ ላይ የነሱን
ጥላቻ እንዳይሰፍርበት እንዲለምን እንዲህ በማለት ያዛል፡፡
{ وَالَّذِينَ جَاءُوا مِنْ بَعْدِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَا
اغْفِرْ لَنَا وَلِإِخْوَانِنَا الَّذِينَ سَبَقُونَا بِالْإِيمَانِ وَلَا
تَجْعَلْ فِي قُلُوبِنَا غِلًّا لِلَّذِينَ آمَنُوا رَبَّنَا إِنَّكَ رَءُوفٌ
رَحِيمٌ } (الحشر : 10)
እነዚያም ከበኋላቸው የመጡት «ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት ለቀደሙን ወንድሞቻችን
ምሕረት አድርግ፡፡ በልቦቻችንም ውስጥ ለእነዚያ ለአመኑት (ሰዎች) ጥላቻን አታድርግ፡፡ ጌታችን ሆይ! አንተ ርኅሩህ አዛኝ ነህና»
ይላሉ፡፡ (ሀሽር 1ዐ)
ከነቢዩ
صلى الله عليه وسلم ቤተሰቦች መብት ዙሪያም አላህ እንዲህ ይላል
{ قُلْ لَا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ أَجْرًا إِلَّا
الْمَوَدَّةَ فِي الْقُرْبَى } (الشورى : 23)
«በእርሱ (መልክቴን በማድረሴ)
ላይ በዝምድና ውዴታን እንጅ ዋጋን አልጠይቃችሁም» በላቸው፡፡ (ሹራ 23)
የዚህን አንቀጽ ትርጉም ሲናገገሩ ዑለማዎች እንዲ ብለዋል “ለአማኝ
ተከታዮችህ ለእኔ ይዤላችሁ ለመጣሁት ምትክ ቤተሰቤን እንድትወዱ እንጂ ደሞዝ አልፈልግም” በላቸው ማለት ነው፡፡
ሙስሊም
ከዘይድ ኢብን አርቀም እንደአስተላለፉት ነቢዩ صلى الله عليه
وسلم እንዲህ ብለዋል “እናንተ
ሰዎች ሆይ እኔ ሰው እስክሆንኩ የጌታዬ መልዕክተኛ መጥቶብኝ ምላሽ ልሰጥ እችላለሁ (መሞቴ አይቀርም) ስለዚህ ለእናንተ ሁለት ታላላቅ
ነገሮችን እተዋለሁ አንደኛው መመሪያና ብርሃን ያለው መፅሐፍ (ቁርአን) ይህን የአላህ መፅሐፍ አጥብቃችሁ ያዙ” በማለት ስለቁርአን
ብዙ ካነሳሱ በኃላ “ሁለተኛው በቤተሰቦቼ አላህን አውሱ በቤተሰቦቼ አላህን አውሱ በቤተሰቦቼ አላህን አውሱ፡፡”
የነቢዩ
صلى الله عليه وسلم ቤተሰቦች የተከበሩና ለነቢዩ صلى
الله عليه وسلم የቀረቡ በመሆናቸው እንዲናከብራቸውና
ደረጃቸውን እንዲንጠብቅላቸው አዘዙ፡፡ እንዲሁም ሰሃባዎችን እንድናከር እነሱን ከመስደብና ከማዋረድ እንድንጠነቀቅ እንዲህ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
« لا تسبوا
أصحابي فلو أن أحدكم أنفق مثل أحد ذهبًا ما بلغ مد أحدهم ولا نصيفه »
“ሰሃቦቼን አትስደቡ እናንተ የኡሁድ ተራራ አምሳያ ወርቅ ብትለቅሱ
እንኳን የሰሃቦች አንድ እፍኝ እንደውም ግማሹንም አይስተካከልም፡፡” (ቡኻሪ 3673 ሙስሊም 2541)
ሰሃቦችንና
የነቢዩ صلى الله عليه وسلم ቤተሰቦች ማክበርና መውደድ የሱና ተከታዮች መለያ የሆነ ዋና መሰረት ሲሆን እነሱን መጥላትና ማውረድ የጥመት
መለያ ነው፡፡
ኢማም አቡ ዘርዓህ እንዲህ ይላሉ :-
“አንድ ሰው ሰሃቦችን ሲያነውር ከገጠመህ መናፍቅ መሆኑን እወቅ፡፡”
ኢማም አህመድም እንዲህ ይላሉ :-
“አንድ ሰው የአላህ መልዕክተኛ ሰሃቦችን በክፉ ሲያነሳ ከገጠመህ
እስልምናውን ተጠራጠር፡፡” ከላይ የተጠቀሱት ለነቢዩ መብት መፈፀም ካለባቸው ተግባራት የተወሰኑት ናቸው፡፡
No comments:
Post a Comment