ለልጆችህ በራስ የመተማመን ስነ-ልቦና ለመገንባት
@ ልጅህን
በሠዎች ፊት አሞግሠው ፡፡
@ ልጅህ
ጥሩ ነገር ሲሰራልህ ፣ ያዘዝከውን ሲፈጽም አመስግናለሁ በለው ፡፡
@ አንድ
ነገር አንዲፈጸም ስትፈልግ ቀጥተኛ ትዕዛዝ አታድርግበት ከተመቸህ ይህን እቃ ታቀብለኝ እቃዎችህን በስርዓት ብታስቀምጣቸው ጥሩ ነው
ይህን የመሠሉ አገላለጽ ተጠቀም፡፡
@ ልጅህ
ልጅነቱን እንዲያጣጥም እድል ስጠው ልጅነቱን እንዲኖር ፍቀድለት፡፡
@ በራሱ
ምርጫውን እንዲወስንና አቋም የመያዝ ክህሎቱን እንዲያዳብር ድጋፍ አድርግለት ፡፡
@ ትላልቅ
ጥሪዎች ሲኖሩህ ቁም ነገር ያላቸው ከፍተኛ ቦታዎች ስትሄድ በቻልከው አቅም አብሮህ እንዲሆን አድርገው ከሁሉም በላይ ልጅህን ይዘህ
ልትሄድ የሚገባው ትልቅና ቁም ነገር ያለው ቦታ መስጅድ ነው።
@ ሐሳብህን
አካፍለው ፤ የርሱንም ሐሳብ ጠይቀው ሀሳቡ ከዲን የወጣ እስካልሆነ ድረስ ተቀበለው፡፡
@ በቤት
ውስጥ ዐቅም በፈቀደ መጠን የራሱ ክፍል ፣የራሱ ቦታ እንዲኖረው አድርግ ፡፡
@ ጥሩ
ጓደኞች እንዲያፈራ ድጋፍ አድረግለት በጓደኞቹ ፊት አትውቀሰው ክብር ስጠው፡፡
@ አላህ
ብዙ ችሎታዎችን እንደለገሰው ንገረው ተፈላጊ እና ቦታ የሚሠጠው እንደሆነ እንዲሠማው አደርገው ፡፡
@ ሶላትን
አስተምረው አብሮህ እንዲሠግድ አድረግ፡፡
@ በዋነኝነት
አላህን እንዲወድ አድርገው ኢማን በልቡ ውስጥ ለማስገባት ጥረት አድርግ ፡፡
@ በአላህ
ላይ መመካትን አስተምረው በራስ የመተማመን ስሜቱ በአላህ ላይ ከሚኖረው መደገፍ የመነጨ መሆን እንደሚገባው አስረዳው።
@ ሐሳቡን
እንዴት መግለጽ እንደሚችል አስተምረው ሐሳቡን ያለፍርሃት መግለጽ እንዲችል አደፋፍረው ስርዓትን አስተምረው
@ በሠዎች
ፊት አትናገር አትበለው ሀሳቡን በማቋረጥ አታሸማቀው።
@ ራሱን
ማክበርና ሰዎችን ማክበር እንዴት እንደሚችል አስተምረው ፡፡
@ ጥያቄዎቹን
መልስለት፣ ልጅነው ብለህ ቸል አትበለው ፡፡
@ የገባህበትን
ቃል አክብር ቃልህን ማክበር የማትችልበት ሁኔታ ከተፈጠረ ቀደም ብልህ አስረዳው ይቅርታም ጠይቀው፡፡
@ ቢያንስ
ብቻውን ቢሆን ለራሱ ምግብ ማቅረብ የሚችልበትን ያህል ማብሰል አስተምረው ፡፡
@ ዘወትር
ዱዓ ማድረግ እንደሚኖርበት አስተምረው። ሲጨንቀው ወደ አላህ መሸሽ እንዳለበት አስረዳው፡
@ ከሌሎች
ልጆችና ከወንድሞቹ/ ከአህቶች ጋር በጋራ መስራትን አስለምደው በቡድን ውስጥ እንዴት ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አሳየው፡፡
@ የተለያዩ
ምክንያቶች በመደርደር ከሠዎች አታርቀው። ሰዎችን መቅረብ የሚወድ አድርገው ፡፡
@ ጥያቄ
እንዲጠይቅ አበረታታው የሚሠነዝራቸውን ጥያቄዎችን «ምን አይነት ጥያቄ ነው»
የሚል መልስ በመስጠት አታሸማቀው
ከተሳሳተ ስህተቱን አስረዳው ፡፡
@ እርሱን
በተመለከተ በምትወስዳቸው ውሳኔዎች ላይ አማክረው፤ ሐሳቦችንና ፍላጎቶቹን አዳምጥ። እርሱ ምን ያውቃል ልጅ ነው ብልህ ፍላጎትህን
ብቻ ልትጭንበት አትሞከር።
@ ስለራስህ
አጫውተው። በአባቱና በእናቱ ደስተኛ ልጅ እንዲሆን አደርግ።
@ እሺ
ማለት ብቻ ሳይሆን የማይስማማውና የማይወደው ነገር ሲኖር እንዴት
እምቢ አይሆንም እንደሚል አስተምረው ፡፡
@ ሲወድቅ
ራሱን ችሎ እንዴት መነሳት እንዳለበት አስተምረው፡፡
@ የራሱን
ክፍል፣ የራሱን ልብሶች፣ እንዲሁም የራሱን የትምህርት መገልገያዎች ራሱ እንዲያስተካክልና በስርዓት እንዲይዝ አስተምረው ፡፡
@ ስለ
ዓላማው ፣ ስለ ህልሙ፣ ስለምኞቱ አዋራው። ሐሳብህን አካፍለው።
@ ኃላፊነቶችን
እንዲወስድ አድርግ፡፡
@ ስራዎችን
ሲያጠናቀቅ አወድሰው። የማበረታቻ ሽልማቶች ስጠው፡፡
@ ጥፋት
ስትፈጽምበት ይቅርታ ጠይቀው፡፡
@ ልዩና
አስደሳች ስጦታዎችን ባልጠበቀው ሠዓትና ቦታ ስጠው።
@ ከቁርዓን
ጋር ያለው ግንኙነት የጠበቀ እንዲሆን አድርግ ፡፡
@ ስለሶሀቦች
የህይወት ታሪክ መፅሀፎችን አንብብለት ፤ ምን ያህል መንፈሰ ጠንካራ መልካም ሰዎች እንደነበሩ አስተምረው፡፡
@ መፅሀፍቶችን
እንዲያነብ አበረታታው። በንባብ በሚያገኘውን ዕውቀት በራስ የመተማመን ስነ ልቦናውን እንዲዳብርለት አድርግ ።
@ ዘወትር
ዱዓ አድርግለት። አላህን መልካሙን መንገድ እንዲያመላክተው ከክፋት ሁሉ እንዲጠብቀው በወላጅ ልብ ተማፀንለት። ሁሉም መሆን የሚችለው
በአላህ ሀይልና ፍቃድ ብቻ ነው።
No comments:
Post a Comment