በቁርአን ማመንና መለያዎቹ 2...
በማስከተል አምሳያው የሆኑ አስር ምዕራፎችን እንዲያመጡም
ቢሞክራቸው አልቻሉም፡፡
{ أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ قُلْ فَأْتُوا بِعَشْرِ سُوَرٍ
مِثْلِهِ مُفْتَرَيَاتٍ وَادْعُوا مَنِ اسْتَطَعْتُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ إِنْ
كُنْتُمْ صَادِقِينَ } (هود : 13)
ይልቁንም «(ቁርኣንን) ቀጣጠፈው» ይላሉን? «እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን ዐስር የተቀጣጠፉ ሱራዎች አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን (ረዳት) ጥሩ» በላቸው፡፡ (ሁድ 13)
ከዚያም በሶስተኛው አምሳያው የሆነ አንድ ምዕራፍ
እንኳን እንዲያመጡ ቢሞክራቸውም አልቻሉም፡፡
{ أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ قُلْ فَأْتُوا بِسُورَةٍ مِثْلِهِ
وَادْعُوا مَنِ اسْتَطَعْتُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ }
(يونس : 38)
በእውነትም «(ሙሐመድ) ቀጣጠፈው» ይላሉን᐀ «ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት) ሱራ አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ
የቻላችሁትን ሁሉ (ረዳት) ጥሩ፡፡ እውነተኞች እንደሆናችሁ (ተጋግዛችሁ አምጡ)» በላቸው፡፡ (ዩኑስ 38)
ከቁርአን ትንሹ ምዕራፍ ባለሶስት አንቀፅ ምዕራፍ ሲሆን
ይህንን እንኳን ተመሳሳዩን ማምጣት የማይችሉ መሆናቸው የቁርአንን ኃያልነት ያረጋግጣል፡፡
አላህ በቁርአን አማካኝነት ለሰዎች ለሃይማኖታቸውም ሆነ
ለአለማዊ ህይወታቸው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ገልጿል፡፡
{ وَنَزَّلْنَا عَلَيْكَ الْكِتَابَ تِبْيَانًا لِكُلِّ شَيْءٍ
وَهُدًى وَرَحْمَةً وَبُشْرَى لِلْمُسْلِمِينَ } (النحل : 89)
‹‹መጽሐፉንም ለሁሉ ነገር አብራሪ፣ መሪም፣ እዝነትም፣ ለሙስሊሞችም አብሳሪ ኾኖ ባንተ ላይ አወረድነው፡፡›› ነህል 89
{ مَا فَرَّطْنَا فِي الْكِتَابِ مِنْ شَيْءٍ } (الأنعام : 38)
‹‹በመጽሐፉ ውስጥ ምንንም ነገር አልተውንም ›› አል አንዓም 38
ኢብን
መስዑድ እንዲህ ይላሉ “በቁርአን ሁሉም እውቀቶች ወርደዋል ማንኛውም ነገር ቁርአን ውስጥ ተዘርዝሮልናል፡፡”
አላህ
ይህን ቁርአን ለአስተንታኞች ገር በማድረግ አቅሎታል፡፡ ይህ ደግሞ ከጐሉ የቁርአን መለያዎች አንዱ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል
{ وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِنْ
مُدَّكِرٍ } (القمر : 17)
‹‹ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም
አልለን?›› አል ቀመር 17
{ كِتَابٌ أَنْزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ
لِيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ } (ص : 29)
‹‹(ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን
እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡›› ሷድ 29
ሙጃሂድ
የመጀመሪያውን አንቀፅ ስያብራሩ እንዲህ ይላሉ :- “የቁርአን አነባብ ገር አደረግን
ማለት ነው፡፡”
ሱድይም እንዲህ ብለዋል:- “ አነባቡን ምላስ ላይ
ቀለል እንዲል አደረግን፡፡”
ኢብኑ ዓባስም እንዲህ ይላሉ :- “አላህ የቁርአን አነባብን ለሰዎች ምላስ እንዲቀል ባያደርግ ኖሮ
የትኛውም ፍጡር የአላህን ንግግር ማንበብ አይችልም ነበር፡፡”
ጠበሪይና
ሌሎችም የቁርአን ተርጓሚዎች እንዳሉት የቁርአን ገር መሆን አነባቡንም ትርጉሙንም የሚመለከት ነው፡፡ ሲነበብ ለምላስ ቀለል
እንዲል ትርጉሙንም ለማስተንተንና በትርጉሙም ለመመከር የተገራ ነው፡፡
8 ቁርአን ከበፊቱ የነበሩትን መፃህፍት ትምህርቶች ጨምቆ የያዘ ነው፡፡ አላህ
እንዲህ ብሏል
{ وَأَنْزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِمَا
بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ الْكِتَابِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ } (المائدة : 48)
‹‹ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡›› አል ማኢዳህ 48
{ شَرَعَ لَكُمْ مِنَ الدِّينِ مَا وَصَّى
بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ
وَمُوسَى وَعِيسَى أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ } (الشورى :
13)
‹‹ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ
ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)፡፡›› ሹራ 13
ቁርአን የቀድሞዎችን ነቢያትና ህዝቦቻቸውን ታሪክ
ባልተለመደ ልዩ ሁኔታ የሚተርክ ነው፡፡
{ وَكُلًّا نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنْبَاءِ الرُّسُلِ مَا
نُثَبِّتُ بِهِ فُؤَادَكَ } (هود : 120)
‹‹ከመልክተኞቹም ዜናዎች (ተፈላጊውን) ሁሉንም ልብህን በርሱ የምናረካበትን እንተርክልሃለን፡፡›› ሁድ 12ዐ
{ ذَلِكَ مِنْ أَنْبَاءِ الْقُرَى نَقُصُّهُ
عَلَيْكَ مِنْهَا قَائِمٌ وَحَصِيدٌ } (هود : 100)
‹‹ይህ (የተነገረው) ከከተሞቹ ወሬዎች ነው፡፡ ባንተ ላይ እንተርከዋለን፡፡ ከእርሷ ፋናው የቀረና ሙሉ በሙሉ የተደመሰሰ
አለ፡፡›› ሁድ 1ዐዐ
{ كَذَلِكَ
نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنْبَاءِ مَا قَدْ سَبَقَ وَقَدْ آتَيْنَاكَ مِنْ لَدُنَّا
ذِكْرًا } (طه : 99)
‹‹እንደዚሁ በእርግጥ ካለፉት ወሬዎች ባንተ ላይ እንተርካለን፡፡ ከእኛም ዘንድ ቁረኣንን በእርግጥ ሰጠንህ፡፡›› ጣሃ 99
ቁርአን ከመጨረሻው የመደምደሚያው ላለፉት መስካሪ የሆነ መፅሐፍ
ነው፡፡
{
نَزَّلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ
وَأَنْزَلَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنْجِيلَ }{ مِنْ قَبْلُ هُدًى لِلنَّاسِ
وَأَنْزَلَ الْفُرْقَانَ } (آل عمران : 3 ، 4)
‹‹ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን
(ቁርኣንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል፡፡ (ከቁርኣን) በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ
(አወረዳቸው)፡፡ ፉርቃንንም አወረደ ፡፡›› (አል ዒምራን 3-4)
{ وَأَنْزَلْنَا إِلَيْكَ
الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ الْكِتَابِ
وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ } (المائدة : 48)
‹‹ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡›› አል ማኢዳህ 48
እነዚህ ከፊል ቁርአንን ከሌሎች መፃህፍት የሚለይ መለያዎቹ ሲሆኑ በቁርአን
ላይ ያለን እምነት እንዲረጋገጥ ወሳኝ ነጥቦች ናቸው፡፡
No comments:
Post a Comment