Tuesday, 21 February 2017

ጤናማ ትዳር

ጤናማ   ትዳር

   የትዳር ህይወት ጤናማ እንደሆነ ሶስት መሠረታዊ ነጥቦች አሉ። የሠከነ እና ለተጣማሪዎቹ ሠላማዊ ህይወት የሚመግብ ትዳር እነዚህን ሶስት መሠረታዊ ነገሮችን ሟሟላት አለበት።

1 ሙገሳና አክብሮት 

   ጤናማ የትዳር ህይወት ብዙ ጥረት ይፈልጋል። ጤናማነቱ እያበበና እያደገ እንዲሄድ ደግሞ ጥረቱ መቋረጥ የለበትም። ይህም ሆኖ ፈተናዎች ችግሮች ማጋጠማቸው አይቀርም። በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለማለፍ ደግሞ በባልና በሚስት መካከል መከባበር መኖር አለበት። ባልና ሚስት እርስ በርሳቸው የሚለዋወጡበት አክብሮትና ሙገሳ ከፍተኛ ስነ ልቦና ጠንካሬን ይፈጥርላቸዋል። በመሀላቸውም ጠንካራ መተማመን ያብባል። በዚህ ታግዘው ከችግሮቻቸው በአላህ ፈቃድ ሊወጡ ይችላሉ። ሙገሳና አክብሮት መለዋወጥ ለትዳር ህይወት ጤናማነት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በላትዳሮች ችላ ሊሉት አይገባም። የትዳር ጤናማነትም ይጠቁማል።

2 ለትዳር አጋር መልካም መመኘት

 ለትዳር አጋሩ መልካም መመኘት የማይወድ ሠው አለ የሚለውን ለማመን  ይከብዳል። ነገር ግን በአሳዛኙ ጤንነቱን ባጣ የትዳር ህይወት ውስጥ ይህን ይህን አይነት ችግር ሊከሰት ይችላል። በትዳር ተጣማሪዎች መካከል ጥላቻና ሌላውን የመጉዳት ስሜት ሊኖር አይገባም።ይህ ስሜት ካለ ትዳሩ በሽተኛ ነው። በጣም አደገኛም ስለሆነ አስቸኳይ ህክምና ያስፈልገዋል።

3 ምስጢር ከቤት አለማውጣት

የቤት ውስጥ ምስጢሮች ሾልከው በየስፍራው የሚገኙበት ትዳር ጤናማ አይደለም። ጤናማ ሊሆንም አይችልም፤ ጤንነቱን ለማስመለስም ይከብደዋል። ጤናማ የትዳር ህይወት ለትዳር ውስጥ ምስጢሮች ከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ ይሠጣል። የቤት ችግሮች ምንም ያህል ቢገዝፉ አደባባይ አያወጣቸውም። ምስጢርን የመጠበቅ ይህ ሁኔታ ትዳሩ ጤናማ መሆኑን ከማሳየቱም ባሻገር በባልና በሚስት መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር ያሳያል። ኢስላም የቤት ውስጥ ምስጢሮች መጠበቅና ባልና ሚስት ጋር መቅረት እንዳለባቸው የጠበቀ መርህ አስቀምጧል። ይህ መርህ በትዳር ውስጥ በተግባር መተርጎም አለበት። የሠከነ ትዳር ለማግኘትም መሠረታዊ ነጥብ ነው። 

No comments:

Post a Comment