ትዳርን የሚያናጉ 4 ምክንያቶች
በርካታ ጉዳዩች ትዳርን የሚያፈርሱ ምክንያቶች ይሆናሉ። በተለይ አራት
ምክንያቶች በትዳር ውስጥ ከተከሠቱ በትዳሩና በፍቺ መካከል የሚኖረው ርቀት ቅርብ ይሆናል። የትዳርን ውድቀት ያፋጥናሉ። የሚከተሉት
ናቸው።
ንቀት
አንድ ሙስሊም በፍጹም ሙስሊምን ሊንቅ አይገባም ንቀት አንድን ሠው ለጀሀነም ሊዳረግ የሚችል በቂ መጥፎ ተግባር ነው። ንቀት
የትዳርን ህይወት የመበጥበጥና የማፍረስ ዓቅሙ ከፍተኛ ነው። ጥላቻን ይወልዳል። መርዝ ያመነጫል። ንቀት በቃላት ብቻ ሳይሆን በፊትና
በእንቅስቃሴም የሚገለጽ ስሜት ነው። በየትኛውም መንገድ መወገዝ አለበት።
ትችት ( የመረረ ነቀፌታ)
በትዳር ውስጥ ብዙ ችግሮች ሊከሠት
ይችላል። በዚህ ወቅት ስርዓት ባለው መንገድ ቅሬታን ማሠማት ችግር አይኖረውም። ሆኖም ግን ቅሬታን በመረረ ትችት መግለጽና ስህተቱንና
ስህተት ፈጻሚውን ደባልቆ በኃይል ቃል መንቀፍ ለትዳር አጋር መጥፎ መልዕክት ያስተላልፋል። ለምሳሌ ሚስት የቤት ቆሻሻዎችን ወደ
ውጪ ሳታወጣ ቀረች። «ረስታ» ሲሆን ተንኮለኛ ስለሆንሽ ነው ያላወጣሽው የሚል ስህተቱን ሳይሆን
ራሷን ( ስህተቱ ላይ ሳይሆን ስህተት ፈጻሚ ላይ ) ያነጣጠረ ቅሬታ መሠንዘር በትዳር ህይወት ውስጥ ችግር ይፈጥራል። በተደጋጋሚም
ሲከሠት ትዳሩ የፍቺ በር ማየት ይጀምራል።
ራስን መከላከል
ችግሩ የእኔ አይደለም፤ የአንቺ ነው። ይህ አገላለጽ በውስጡ ራስን
የመከላከልና ሌላውን በጅምላ የማውገዝ ድባብን ይዟል።አለመግባባት ያባብሳል። በመጨረሻም ወደ ፍቺ በር ያደርሳል። ስለዚህ አለመግባባቶች
ሲፈጠሩ ራስን መከላከያ ድንበር ማስመር ብቻ ሳይሆን የትዳር አጋርን ስሜት ለመረዳት ይበልጥ ጠቃሚ ይሆናል። ሌላውን በማውገዝና
ራስን በማጽዳት የትዳር ዘለቄታ ማረጋገጥ አይቻልም።
ችግሮችን በውይይት አለመቋጨት
ውይይት ማቆም ወይንም በዚህ ርዕስ በፍጹም አልነጋገርም ብሎ ውይይትን አቋርጦ መውጣት፣ ችግሮች እንዳይቋጭ ያደርጋል።
ችግሮች ዘወትር ተንጠልጥለው ይቀጥላሉ። ይህ ሁልግዜ የተከፈተ፣ ያልተከደነ ፣ ያልተቋጨ አጅንዳ ይኖራል። ይህ ሁኔታ የትዳር ህይወትን
ይጎዳል። ችግሮች እንዲከማቹም ደርጋል። በመጨረሻም ለፍቺ ያጋልጣል።
No comments:
Post a Comment