ቁርዓን
የጭንቀት መፍትሄ
ከየትኛውም መንገድ በተሻለ ከቁርዓንና ጋር በሚገባ መተዋወቅ መፍትሄ ነው። የሞከረው በደንብ ያውቀዋል። ጭንቀትን ለማስወገድና
በስፍራው ቃላቶች ሊገልጹት ኃይል የሚሰጣቸውን ነፍስን የሚወዘውዝ እርካታ ለማግኘት ከቁርዓን የተሻለ መንገድ ከቶም የለም። ጭንቀት
ስለማይታወቀው ነገር ከመጠን ባለፈ ማሠብ እንደመሆኑ የሸይጧን ውትወታ ውጤት ነው። ለሸይጧን መፍትሄው ደግሞ አላህን ዘወትር ማስታወስ ነው።
الَّذِينَ
آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِۗ أَلَا بِذِكْرِ
اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ [13:28]
(እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም
አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡ ››(ረዕድ 28 )
በአላህ ላይ ጠንካራ እምነት ያለው ሠው ነገን በመፍራት ለጭንቀት አይንበረከክም። ሁሉም ነገር በአላህ እጅ እንደሆነ ያምናል።
የሚሠጠው ፣ የሚያነሳው ፣ የሚያከብረው ፤ የሚያወርደው አላህ ብቻ ነው።
ከጭንቀት ለመራቅ ሸይጧን ማሸነፍና ወደ አላህ ቅርብ መሆን ያስፈልጋል ስለ አላህ ውሳኔና ቀደር የጎላበት እምነትና እውቀት
ማከማቸት የግድ ይላል። ሀሉም ነገር በአላህ ውሳኔ የሚሆን ነው የማያስጨንቅ ነገር የለም !
No comments:
Post a Comment