የወር አበባ የሚያስገድዳቸው ነገሮች
ገላ ትጥበት፡-
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “የወር አበባ የሚቆይብሽን ጊዜ ያህል ሰላት አቁሚና ከዚያ ታጥበሽ ስገጂ፡፡” (ቡኻሪና
ሙስሊም ዘግበውታል)
አቅመ ሄዋን መድረስ፦ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “ የወር አበባ የምታይ ሴት ያለ ሻሽ
ሰላት ብትሰግድ አላህ አይቀበላትም፡፡” (አቡዳውድ ቲርሚዚይና ኢብኑ ማጃህ)
በዚህ ሀዲስ ላይ የወር አበባ የምታይን ሴት ሂጃብን አስገድደዋታል፡፡ ግዴታ ደግሞ የሚጀምረው ለአቅመ ሄዋን በመድረስ ነው፡፡
ስለዚህ የወር አበባ መምጣት የመድረስ ምልክት ነው ማለት ነው፡፡
ቀን ቀጠሮን በወር አበባ መቁጠር፡- የወር አበባ የምታይ ሴት ባሏ ከፈታት ሁለተኛ ሌላ ከማግባቷ በፊት የምትቆየውን ጊዜ
መቁጠር ያለባት በወር አበባዋ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
وَالْمُطَلَّقَاتُ
يَتَرَبَّصْنَ بِأَنفُسِهِنَّ ثَلَاثَةَ قُرُوءٍ
‹‹የተፈቱ ሴቶችም ነፍሶቻቸውን (ከማግባት) ሦስትን ቁርእ ይጠብቁ፡፡››
(አል
በቀራህ 228)
የማህፀን መጥራት የሚወሰነው በወር አበባ በመቁጠር ነው፡፡
ማሳሰቢያ፦
ሴት ልጅ ከወር አበባዋ ወይም ከወሊድ ደም ፀሐይ ከመጥለቁ በፊት ከፀዳች የዕለቱን ዙህርና አስር ሰላት ቀዷ መስገድ ሲኖርባት
ጐህ ከመቅደዱ በፊት ከፀዳች ደግሞ የሌሉቱን መግሪብና ዒሻ ሰላቶች ቀዷ መስገድ አለባት፡፡ ምክንያቱም ችግሮች በሚገጥሙ ጊዜ የሁለተኛው
የሰላት ወቅት ለአንደኛው ይሆናል፡፡ ይህ የማሊክ ሻፊኢይ አህመድና የአብዛኞች ዑለሞች አቋም ነው፡፡
አብዛኛው ና አነስተኛው
የወሊድ ደም ጊዜ
ለአነስተኛ የወሊድ ደም ጊዜ ገደብ ስለሌለው ያለው ሁኔታ ይወስነዋል፡፡ አንዳንዴ በዝቶ ሌላ
ጊዜ ደግሞ አንሶ ይገኛል፡፡ ብዙን ግን አርባ ቀን ነው፡፡ ቲርሚዚይ እንዲህ ብለዋል “የወሊድ ደም ያለባት ሴት ለአርባ ቀን ሰላት
እንደምታቆም ዑለማዎች ተስማምተዋል፡፡ ነገር ግን ከዚያ በፊት ከፀዳች ታጥባ መስገድ ይኖርባታል፡፡” ኡሙ ሰለማ ባስተላለፉትም ሀዲስ
“በነብዩ (ﷺ) ዘመን የወሊድ ደም ያለባት አርባ ቀን ድረስ ሰላት ከመስገድ ትታቀብ ነበር፡፡” (አቡዳውድ ቲርሚዚይና
ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል)
No comments:
Post a Comment