የባልን ክብርና ስሜት መጠበቅ
መልካም ሚስት ባልዋ የሚወደውንና
የሚያስደስተውን ነገር ጠንቅቃ ታውቃለች የሚያስደስተውንም ነገር ለመፈጸም ዘወትር ቁርጠኛ ናት ባልዋን ማስደሰት ብቻ ሳይሆን እንዳይከፋባትም
ጥንቃቄ ታደርጋለች። ከባልዋ ፍላጎትና ደስታ ፊት ጋሬጣ ሆና የምትቆም ግትር አይደለችም። በባልዋ መከፋት ውስጧ የሚደሰት የቤት
ምስጥም አይደለችም። በባልዋ ላይ የበላይነቷን ለማሳየትም ትዕቢት አይዛትም። የባልዋን ስሜት ትጠብቃለች። ስነ ልቦናው እንዳይጎዳ
እርሱ ለራሱ ከሚያስበው በበለጠ እርሷ ለርሱ ታስባለች። እጅግ የሚያረካት ነገር የትዳር አጋሯን የደስታ ፊት ማየት ነው። ደስታውን
እርሷ የሠራችው ከሆነ ደግሞ እርካታዋ ወደር አይኖረውም።
ዐብደላህ ቢን ጀዕፈር አቡጧሊብ
ለባለትዳር ልጁ የሚከተለውን ምክር መስጠቱን የታሪክ ድርሳናት ጽፈዋል
"ልጄ ሆይ ከቅናት ራሽን ጠብቂ ፤ በትዳር ውስጥ መቅናት የፍቺ ቁልፍ
ነው። ብዙ ቅሬታ አታሳሚ ቅሬታ ጥላቻን ይወልዳል።….
" መልካም ሚስት ባልዋ በቤት በማይኖርበት ግዜው ቢሆን ክብሩን ትጠብቃለች
በነፍሷ እና በንብረቱ ላይ ክህደትን አትፈጽምም። ከራሷ ፍላጎትና ሀቅ ፣ የባሏን ፍላጎትና ሀቅ ለማስቀደም ትመርጣለች ምላሷ አጭር
ነው ባልዋን የሚያስቆጣ መርዝ ቃላቶች አያምራትም።
No comments:
Post a Comment