Tuesday, 21 February 2017

የኢስላማዊው አቂዳ አላማዎች

የኢስላማዊው አቂዳ አላማዎች

የኢስላማዊ እምነት አላማዎች ኢስላማዊውን አቂዳ አጥብቆ በመያዝ የሚገኙት ውድ የሆኑ ግቦች ብዙና የተለያዩ ሲሆኑ ከነሱም መሐከል

አንደኛ፡- ኒያንና (ፍላጐትን) አምልኮትን ለአላህ ማጥራት፡፡ አላህ  ብቸኛ ምንም ተጋሪ የሌለው ፈጣሪ እንደመኑ ፍላጐትና አምልኮትም ለሱ የጠሩ መሆን ይገባቸዋል፡፡

ሁለተኛ፡- ይህንን እምነት በማጣት ከሚከሰት የአእምሮና የአስተሳሰብ ሀብት መጠበቅ፡፡ ልቡ በኢስላማዊው አቂዳ ዉጪ የሆነ ሰው ወይም ምንም አይነት እምነት የሌላው ቁስ አምላለኪ ይሆናል አልያም የተሳሳተ እምነት ውስጥና አፈተረት ውስጥ ይዘፈቃል፡፡

ሶስተኛ፡- በዚህ እምነት የፀና ሰው የነፍስና የአመለካከት መረጋጋትን ያገኛል የነፍስ ጭንቀትም ይሁን የአመለካከት መዛባት አያጋጥሙትም ይህቺ እምነት አማኙ ከፈጣሪው ጋር ታገናኘዋለች ስለሆነም የፈጣሪውን አስተናባሪ ጌትነቱ፣ ደንጋጊ ፈራጅነቱን ይወዳል፣ በውሳኔውም ልቡ ይረጋጋል ለኢስላምም ልቡ ክፍት ይሆናል ተለዋጭም አይፈለግለትም፡፡

አራተኛ፡- በአላህ አምልኮ ላይም ይሁን ከፍጡራን ጋር በመኗኗር ላይ ፍላጐትና ተግባርን ከመዘንበል ማዳን፡፡ ከመሰረቶቹ መሐከል አንዱ ሰላማዊ የነውን መንገዳቸውን ከመከተል ጋር በመልዕክተኞች ማመን ነውና፡፡

አምስተኛ፡- በነገሮች ላይ በአጠቃላይ ቆራጠኛና ትጉህ መሆን፣ የአላህን ምንዳ በመከጀል የመልካም ስራን አጋጣሚ በሚያሳልፍበትና የአላህን ቅጣት በመፍራት የወንጀልን መውደቂያዎች ሁሉ በሚርቅበት ደረጃ ከኢማን መሰረቶች አንዱ ከሞት በኃላ መቀስቀስ በሰሩት መመንዳት በመኖሩ ማመን ነውና፡፡

﴿ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُواْ وَمَا رَبُّكَ بغَافِلٍ عَمَّا يَعْمَلُونَ[سورة الأنعام : 132]

ለሁሉም ከሠሩት ሥራ (የተበላለጡ) ደረጃዎች አልሏቸው፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡” አል አንዓም 132
ወደዚህ ግብም ነብዩ በተከታዩ ንግግራቸው አነሳስተዋል

(المؤمن القوي خيرٌ ، وأحب إلى الله من المؤمن الضعيـف ، وفي كل خير ، احرص علـى ما ينفعـك ، واستعن بالله ، ولا تعجز ، وإن أصابك شيء فلا تقل : لو أنِّي فعلت كذا كان كذا وكذا ، ولكن قلْ : قدَّر الله وما شاء فعل ؛ فإن (لو) تفتح عمل الشيطان )

ጠንካራው አማኝ ከደካማው የበለጠ አላህ ዘንደ በላጭና ተወዳጅ ነው፡፡ ሁለቱም መልካም ነገር አላቸው የሚጠቅምህ ነገር ላይ ትጉ ሆነህ በአላህ ጋዝ አትዳከም የማትወደው ነገር ቢደርስብህ እንዲህ ባረግ እኮ እንዲህ እንዲህ ይሆን ነበር አትበል ነገር ግን አላህ ወሰነ የፈለገውንም ፈፀመ በል ቢሆን ኖሮ የሸይጣንን በር ትከፍታለች፡፡”

ስድስተኛ፡- ውዱንም ይሁን እርካሹን ንብረቱን ሃይማኖቱን መሰረቶቹንም ለማጠንከር ለማፅናት የሚሰዋ በዚህ መንገድ ለሚደርስበት ችግርም የሚታረስ ጠንካራ ማህበረሰብ መመስረት ለዚህም አላህ እንዲህ ይላል

﴿ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثـُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبيلِ اللَّهِ أُوْلَئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ)[سورة الحجرات : 15]

እውነተኛዎቹ) ምእምናን እነዚያ በአላህና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶ ቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፡፡ እነዚያ እነሱ እውነተኞቹ ናቸው፡፡” ሁጅራት 15

ሰባተኛ፡- ግለሰቦችንም ይሁን ማህበረሰቡን ለማስተካከል፣ ለምንዳና ለቀብር ለቅርቢቱ አለምም ይሁን ለወዳኛው አለም እድለኝነት ማብቃት፡፡ ይህንን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል

﴿ مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذكَرٍ أَوْ أُنثَى وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بأَحْسَنِ مَا كَانُواْ يَعْمَلُونَ[سورة النحل : 97

ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡” አል ነህል 97


እነዚህ ከፊል የእስልምናው እምነት አላማዎች ሲሆኑ ሁሉንም አላማዎች ለእኛም ለሙስሊሞችም በአጠቃላይ አላህ እንዲያረጋግጣቸው እንከጅላለን፡፡

No comments:

Post a Comment