ህዝቦች ላይ ግዴታ የሆኑ የነቢዩ صلى
الله عليه وسلم መብቶች
ኡማው ላይ ዋጂብ የሆኑ የነቢዩ
صلى الله عليه وسلم መብቶች ብዙ ናቸው፡፡ ጥቂቶችን የሁሉም ነቢያት መብቶችን
ስንጠቅስ በጥቅሉ የጠቀስን ቢሆን ከዚህ ርዕስ ስር ነቢዩን በተለየ መልኩ የሚመለከት መብቶቻቸውን እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡
1 በሳቸው ነቢይነት በዝርዝር በማመነ የሳቸውን መልዕክት የቀድሞ መልዕክተኞችን ሁሉ በመሻር
የተቀየራ መሆኑን መቀበል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
{ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ
وَالنُّورِ الَّذِي أَنْزَلْنَا } (التغابن : 8)
‹‹በአላህና በመልክተኛውም፡፡ በዚያም ባወረድነው ብርሃን እመኑ፡፡››
ተጋቡን 8
{ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ
النَّبِيِّ الْأُمِّيِّ الَّذِي يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَكَلِمَاتِهِ وَاتَّبِعُوهُ
لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ } (الأعراف : 158)
‹‹በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ
ነቢይ በኾነው መልክተኛው እመኑ፡፡ ቅንንም መንገድ ትመሩ ዘንድ ተከተሉት፡፡»
አል አዕራፍ 158
{ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا
نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانْتَهُوا } (الحشر : 7)
‹‹መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም
የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡›› አል ሀሽር 7
2 ነቢዩ صلى الله عليه
وسلم መልዕክትን እንዳደረሱ አደራን
እንደተወጡና መልካም የተባለን ሁሉ በመጠቆምና ክፋትን ሁሉ በመከልከል መልካም ምክርን እንደለገሱ ማመን፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
{ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ
عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا } (المائدة : 3)
‹
‹ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን
ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡›› አል ማኢዳህ 3
አቡዳርዳእ እንዳስተላለፉት ነቢዩ صلى
الله عليه وسلم እንዲህ
ብለዋል
« وأيم
الله لقد تركتكم على مثل البيضاء ، ليلها ونهارها سواء»
“በአላህ እምላለሁ ነጭ በሆነና ሌሊቱና ቀኑ አንድ በሆነ በግልፅ መንገድ ላይ ነው የተውኳችሁ፡፡” (ኢብኑ ማጃህ 5)
ነብዩ
صلى الله عليه وسلم መልዕክታቸውን እንዳደረሱ ሰሃቦች ነቢያችን صلى
الله عليه وسلم የመሰናበቻ ሀጅ ባደጉበት
ታላቅ ስብሰባ ላይ መስክረውላቸዋል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ ነቢዩ صلى
الله عليه وسلم ግዴታዎችንና ክልከላዎችን
ዘርዝረው በቁርአን ከመከሩ በኃላ ሰሃቦችን እንዲህ አሏቸው “ስለ እኔ ስትጠየቁ መልሳችሁ ምን ይሆናል? እነሱም መልዕክቱን እንዳደረሰ
ኃላፊነቶን እንደተወጡና እንደመከሩ እንመሰክራለን፡፡ አሉ” ነቢዩም
صلى الله عليه وسلم አመልካች ጣታቸውን ወደ ሰማይ ጠቁመው ወደ ሰዎች በማውረድ ሶስት ጊዜ “ጌታዬ ሆይ መስክር” አሉ፡፡ (ሙስሊም
1218)
አቡዘር እንዲህ ይላሉ
“ሙሐመድ صلى
الله عليه وسلم ከእውቀት ምንም አላስቀሩብንም
ወፍ እንኳን ክንፋን እያርገበገበ አይር ላይ ሲበር ከሱ ጋር የተያያዘ እውቀት ያማውቁን ነበር፡፡” (አህመድ 5/153)
በዚህ ርዕስ ከቀደምት አበዎች የተዘገቡ ዘገብዎች ብዙ አሉ፡፡
3 ነቢዩን صلى
الله عليه وسلم ከማንም ፍጡር ላይ ከራስም
ጭምር አስበልጦ መውደድ፡፡ ነቢያትን መውደድ በጥቅሉ ግዴታ ቢሆንም ነገር ግን ነቢዩን صلى
الله عليه وسلم ከሌሎች ነቢያት ፍቅር በበለጠ
ከአጠቃላይ ህዝብ ከዘመድ አዝማድ ከራስም ጭምር አስበልጦ መውደድ ግዴታ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
{ قُلْ إِنْ كَانَ آبَاؤُكُمْ وَأَبْنَاؤُكُمْ وَإِخْوَانُكُمْ
وَأَزْوَاجُكُمْ وَعَشِيرَتُكُمْ وَأَمْوَالٌ اقْتَرَفْتُمُوهَا وَتِجَارَةٌ
تَخْشَوْنَ كَسَادَهَا وَمَسَاكِنُ تَرْضَوْنَهَا أَحَبَّ إِلَيْكُمْ مِنَ اللَّهِ
وَرَسُولِهِ وَجِهَادٍ فِي سَبِيلِهِ فَتَرَبَّصُوا حَتَّى يَأْتِيَ اللَّهُ
بِأَمْرِهِ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ } (التوبة : 24)
«አባቶቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁም፣ ሚስቶቻችሁም፣ ዘመዶቻችሁም፣
የሰበሰባችኋቸው ሀብቶችም፣ መክሰሩዋን የምትፈሩዋት ንግድም፣ የምትወዷቸው መኖሪያዎችም እናንተ ዘንድ ከአላህና ከመልክተኛው በርሱ
መንገድም ከመታገል ይበልጥ የተወደዱ እንደኾኑ አላህ ትእዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ»
በላቸው፡፡ አላህም አመጸኞች ሕዝቦችን
አይመራም፡፡ (አል ተውባህ 24)
ቡኻሪና መስሊም ከአባስ በአስተላለፉት ሀዲስ ነቢዩ صلى
الله عليه وسلم እንዲህ
ብለዋል
« لا يؤمن
أحدكم حتى أكون أحب إليه من والده وولده والناس أجمعين »
“እናንተ ዘንድ ከወላጅ ከልጃችሁና ከሁሉም ሰው በላይ ተወዳጅ እስካልሆንኩ
እምነታችሁ የተስተካከለ አይሆንም፡፡” (ቡኻሪ 15 ሙስሊም 49)
በአንድ ወቅት ዑመር ለነቢዩ صلى الله عليه وسلم “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ እርሶን ከነፍሴ ብቻ አላስበልጦ እንጂ ከሁሉ ነገር በላይ እወዳታለሁ” ሲላቸው
“በፍፁም ነፍሴ በእጄ ባለው እምላለሁ ከራስህ አስበልጦህ እስካልወደድከኝ ኢማንህ ገና ነው” አሉት ዑመርም እንዲህ አላቸው “አሁን በአላህ እምላለሁ ከነፍሴ አስበልጬ እወዶታለሁ” ነቢዩም صلى الله عليه وسلم “አሁን ገና ዑመር” አሉት፡፡” (ቡኻሪ 6632)
4 ነቢዩን صلى
الله عليه وسلم ማላቅና
ማክበር፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
{ لِتُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَتُعَزِّرُوهُ
وَتُوَقِّرُوهُ } (الفتح : 9)
‹‹በአላህ ልታምኑ፣ በመልክተኛውም (ልታምኑ)፣ ልትረዱትም፣ ልታከብሩትም››
ፈትህ 9
{ فَالَّذِينَ آمَنُوا بِهِ وَعَزَّرُوهُ وَنَصَرُوهُ
وَاتَّبَعُوا النُّورَ الَّذِي أُنْزِلَ مَعَهُ أُولَئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ }
(الأعراف : 157)
‹‹እነዚያም በእርሱ ያመኑ ያከበሩትም የረዱትም ያንንም ከእርሱ ጋር
የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ እነዚያ እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡›› አል አዕራፍ 157
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُقَدِّمُوا بَيْنَ
يَدَيِ اللَّهِ وَرَسُولِهِ } (الحجرات : 1)
‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልክተኛው ፊት (ነፍሶቻችሁን) አታስቀድሙ፡፡››
ሁጅራት 1
{ لَا تَجْعَلُوا دُعَاءَ الرَّسُولِ بَيْنَكُمْ كَدُعَاءِ
بَعْضِكُمْ بَعْضًا } (النور : 63)
‹‹በመካከላችሁ የመልክተኛውን ጥሪ ከፊላችሁ ከፊሉን እንደ መጥራት አታድርጉት፡፡››
ኑር 63
ሙጃሂድ ይህን አንቀጽ ሲያብራሩ “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ብለው
በዝግታና በስርአት እንዲጠ ሯቸዉ በማዘዝ አንተ ሙሐመድ ብለው እንዳይጠሯቸው ከለከለ፡፡ ሰሃቦች ነቢዩን صلى الله عليه وسلم በማክበር ተመሳሌት እንደነበሩ የኢማም ኢብን ሸሪክ ንግግር ይጠቁማል “አንድ ጊዜ ወደ ነቢዩ صلى الله عليه وسلم ስሄድ በዙሪያቸው ሰሃቦች ራሳቸው ላይ ወፍ እንዳለ ሆነው ተቀምጠው አገኘሁ፡፡”
ነቢዩን صلى
الله عليه وسلم ማላቅ በህይወቱ እያሉ ግድ
እንደሆነ ሁሉ ከሞቱም በኃላ እሳቸውን ማክበር ግዴታ ነው፡፡ ቃዲ ዒያድ እንዲህ ይላሉ “የነቢዩን صلى الله عليه وسلم ክብር መጠበቅና የላቀ አክብሮት መለገስ ከሞቱም በኃላ ቢሆን በህይወት ሳሉ ግድ እንደሆነው ሁሉ ግዴታ ነው፡፡
ከሞቱ በኃላ እሳቸውን ማክበር የሚገልፀው እራሳቸው በሚወሱበት ጊዜ፣ ሀዲስና ሱናቸው ሲነገር፣ ስማቸውና ታሪካቸው በሚደመጥ ጊዜ
ነው፡፡ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን፣ ባልደረቦቻቸውንና ዘራቸውንም ማክበር ለአክብሮታቸው መገለጫ ነው፡፡”
No comments:
Post a Comment