ትምህርት ቁጥር 4
ሙስሊሟ ሴት እና facebook
ሙስሊሟን ሴት የእመቤትነት ማእረግ ሊያስጥሏት የሚፈለፈሉ ፈተናዎች ተበራክተዋል። ለአማኟ ሴት ትላንት ቤቷ ውስጥ እንድትረጋ የተላለፈው ኢስላማዊ ድንጋጌ መውጣቷን ተከትሎ ብዙ ችግሮች ስለሚከሰቱ ነበር። ዛሬ ግን ከለሩን ቀይሮ በመጣው ፊትና facebook skype paltalk እና የመሳሰሉት ጥፋት የሚበዛባቸው መስኮቶች ላይ አማኟ ሳታውቀው እንዲያውም በአላም ላይ አካላይ ሆና አንግታለች። መቼም እንደዚህ ስል “ወይ ጉድ ሚጠቅም ጎን የለውም ነው የምትይው???” የሚሉ ጥያቄዎ ች ስፍር ቁጥር እንደማይኖራቸው እገምታለው። ይሁን እሺ ኸይር እንደማመጥ። ጥቅም እንዳለው ባይካድም የጥፋት ጎኑ ግን የደለበ ነው። በእርግጥ እንደሰውየው አጠቃቀምም ሚውስንበት ጊዜ አለ። ለማንኛውም ግን በሴቷ ላይ የሚያደርሰው ጥፋት ከባድ ነው። አዎ! በእርግጠኝነት አንድ ሙስሊም ሴት ምንም የባሰባት ብትሆንም ከቤት ወጥታ በምታደርገው ጉዞዋ ላይ የምታውቀውንም የማታውቀውንም ባእድ (አጅነብይ) ወንድ ቆማ ከሰላምታ አልፎ የባጡን የቋጡን የምትዛላብድ አልነበረችም። ባልተፈቀደ መንገድ የወንድ ጓደኛ በመያዝ የተፈተነች እንኳ እንደው የለየላት ካልሆነች በስተቀር ጓደኛዋን ለማውጋት ቦታና ሁኔታዎችን በመምረጥ ትሽሽግ ትሰወር ነበር።ዛሬ ዛሬ ግን ነገር አለሙ በቀለለና በተራቀቀ መልኩ ከተፍ ያለላት ትመስላለች። እንደትላንቱ ብዙ ውጣ ውረድ አያስፈልጋትም። በመሆኑም ትላንት እንኳ እርቃን በሆነችበት ጊዜ ያልደፈረችውን ዛሬ በቤቷ ተቀምጣ onlin ወደ ሚባለው የጥፋት ቦታ በየቀኑ በየሰአቱ እየተገኘች አለም አቀፍ ወንዶችን ትፈትናለች ታማልላለች። ትላንት በመንገድ ሲለክፏት እንኳ የምትሽኮረመም አሊያ ምን ሲደረግ ተነክቼ በሚል የነብር አራስ ትሆን የነበረችው ዛሬ ዛሬ ግን ምስሏን (በሂጃብም ቢሆን) በመልቀቅ በ comment አማካኝነት የሚመጡ ለከፋዎችን በደስታ በፌሽታ እያጣጣመችው ትገኛለች። “ተገላቢጦሽ” ማለት እንግዲህ ይሄ ነው። አሁንም ጥያቄ ተነስቷል። “እንዴ ጭራሽ onlin አትሁኑ ነው እንዴ የምትይን???” አይደለም። ነገር ግን አስፈላጊ ሲሆን ብቻ ነው መሆን የሚገባው። ለነገሩ ሳይሆኑም አስፈላጊ ነገሮች መሰራት ይችላሉ። post ማድረግ ትችያለሽ። like ማድረግ ትችያለሽ። comment መስጠት ትችያለሽ። ማንበብ ማድመጥ መፃፃፍ ሌላም ሌላም ትችያለሽ። እንግዲህ ይህ ከሆነ ለምን ታዲያ ሃያ አራት ሰአ onlin መሆን ተፈለገ??? መልሱን እራሷን መሸንገል ለማያውቃት እንቁዋ አማኝ እህቴ ትቼዋለው።

ሌላው ችግር ደግሞ ብዙዎቻችን
ላፕቶፑን አሊያ ሞባይሉንና ወዘተ ብቻ አይደለም onlin የምናደርገው። ይልቁንም እኛም ጭምር ነን on የምንሆነው። አላሁል ሙስተዓን።
በእውነቱ ይህን መሰል የጥፋት ቦታ ላይ አማኝ ሴት ነቃ ልትል ይገባል። የውስጥም ይሁን የላይ ጠላቶቿ ኢስላም የቸራትን ማእረግ
ለማስጣል የማይቆፍሩት ጉድጓድ እንደሌለ በወጉ ልትገነዘብ ይገባል። እነዚህንም መሳሪያዎች መጠቀም ካለባትም ተጠቅማ ልትጠቅምበት
በምትችለው ነገር ላይ ብቻ ልታውለው ይጋባል። የበለጠ አላህን ልትፈራበት፤ ምንም ነገር የማይደበቅበትን ተቆጣጣሪነቱን ለአፍታም
ቢሆን የማትዘነጋበት ሊሆን ግድ ይላታል። ይገርማል ጥያቄዎች እንደቀጠሉ ናቸው። “እሺ እኛ ብቻ ነን እንዴ ጥፋተኞች ወንዶቹስ???”
አልወጣኝም። ነገር ግን ይህን ጥያቄ ከመመለሴ በፊት፦ ለጥፋት መንሰኤ በመሆንና ጥፋተኛ በመሆን መካከል ያለው የሰማይና የምድር
ያህል ልዩነት ሌጤን ይገባዋል እላለሁ። አሊያ ደግሞ በሌላ አነጋገር እኛ በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው በየሰከንዱ onlin እየዋልን።
በጎን ደግሞ የchat መስኮት አጣድፎ ገደለን ብንል እንዴት ነው ተቀባይነቱ የሰፋ ሊሆን የሚችለው??። ለምንስ ነው በቂ ምክንያት
ሳይኖረን ወንዶችን የምናናግረው??። አዎ ብዙ ጊዜ ጀማሪዎቹ ወንዶች እንደሆኑ ይገባኛል። ግና ቀጣዮቹና ጨራሾቹ እኛ ከሆንን የጥፋቱን
መጠን መገመት አያዳግትም። ጥፋትን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ባይቻል ራሱ መቀነስ ግን ይቻላል።አስፈላጊ ካልሆነ profile ዝርዝር
መረጃን ግልፅ አለማድረግ። እንዲሁም በሰም ከመግባት መቆጠብ። ሁሉ ነገር ልክ ሲኖረው ነው ሚበጀው። ያለ ጥርጥር በእንደዚህ አይነቶች
የመገናኛ ብዙሃን ላይ ያለው የወንዶች እይታም ለከት ሊኖረው ይገባል። አላህን ሊፈሩበት የግድ ነው። አሁን አሁንማ አላህ ያዘነለት
ሲቀር እነዚህን መሳሪያዎች መጀናጀኒያ እና መተጫጫ ያደረጉት ለቁጥር ታክተዋል። በዚህ መልኩ ለትዳር የመብቃት ስምረትን ሙሉ በሙሉ
ማስተባበል ባልደፍርም ባብዛኛው ግን ከንቱ ድካም ነው። ስንትና ስንት ሴቶች ናቸው እውነተኛ ማንነታቸውን ሳታውቅ በጉጉት የሚያዋዥቁህ።
ወይ ብቸኝነትህን እንዳታስታም አሊያ ትዳርህን እንዳታጣጥም ውጋት የሆኑብህ። ወንድሜ አላህን ልትፈራ ይገባል። እስኪ በአላህ ላፍታ
እንኳ ቆም በልና የህይወት መመሪያ ብርሃኔ ነው ብለህ የምታምንበትን ቁርአንና ሱና እወቀው። አጥናው በጥሞና። አንተ ገና እውነተኛ
ማንነቷ በውል ላልተረጋገጠች ሴት በቻት መስኮት ላይ ውሃ ውስጥ እንደገባ ጨው ትሟሟለህ። የብቃትህ ሃይል ይመክናል።
አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ቁርአኑ ላይ እንደገለፀልን፦እጅግ በጣም ውብ ወጣት፤ እንደፈለጉ ቢያዙትም አቤት ሊል የሚገባው የንጉስ ቤት ነዋሪ፤ በክፍሉ ውስጥ ብቻውን ሆኖ ሳለ። እጅግ በጣም ተውባና ተቆንጅታ የንጉሱ ሚስት ዘው አለችበት። በር ብቻ ሳይሆን በሮቹን ሁሉ ቆላለፈቻቸው። ለእርሱ ስትል ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀችም አበሰረችው። ምንም ስሜትን ከጫፍ የሚያደርሱ ነገሮች ቢመቻቹለትም ራሱን አቅቦ ይህን አጭር መልስ ሰጣት:-
“ "قال معاذ الله" “በአላህ እጠበቃለሁ አላት” ” (ምእራፍ ዩሱፍ 23)
ወንድሜ ሆይ! ለናሙና ያህል ነው ይህን ታላቅ ታሪክ የጠቀስኩልህ። ሙሉውን ምእራፍ በደንብ በማስተንተን አጣጥመው። በህይወትህ ላይ የንፅህናን እሴት ያፈነጥቅልሃል። አዎ በርግጠኝነት ፍቅር ስሜት መፈላለግ ወዘተ ይኖራል። ነገር ግን የዩሱፍ ታሪክ በከንቱ አልተላለፈምና ለአላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ስትል ተወው። ታላቅነቱን የበላይነቱን አስታውስ። ለእርሱ ብለህ ትተህ ደግሞ አላህ በባዶ የሚያስቀርህ ጌታ ፈጽሞ አይደለም። ሙሉውን ታሪክ ወደ ቁርአን ተመልሰህ እንድታጣጥመው ስለከጀልኩ እንጂ የዩሱፍን ያልታሰበና አስደናቂ ሽልማት ባትትልህ ደስ ባለኝ ነበር።
ይህን አስመልክቶ ታላቁ የኢስላም ምሁር ኢብኑ ተይምያህ (አላህ ይዘንለትና) እንዲህ ሲል በወርቅ የሚፃፍ ንግግር ተናግሯል።
«አንድ ሰው) በፍቅር ተፈትኖ ራሱን በጨዋነት ልጓም ካሰረና ከታገሰ በዚህ ለአላህ በሚኖረው ተቅዋው በመልካሙ ይመነዳል። በሸሪዓዊ ማስረጃ እንደሚታወቀው (አንድ ሰው) ከሃራም እይታ፤ ንግግር እንዲሁም ተግባር ራሱን ካቀበ ይህንንም በውስጡ በመያዝ ካልተናገረ ምክንያቱም በዚህ ንግግር ሃራም እንዳይኖርበት (ስለሚሰጋ) ይህም ወይ ወደ ፉጥር እሮሮን በማሰማት ወይም ብልግናን በመናገር ወይም የሚያፈቅረውን አካል በመለመን ሊሆን ይችላል። ታዲያ በአላህ ትእዛዝ ላይ ፤ እርሱን ከመወንጀል በመታቀብ ላይ እንዲሁም በልቡ ውስጥ ባለው የፍቅር ህመም ላይ ልክ ችግር የደረሰበት ሰው ችግሩ ላይ እንደሚታገሰው ሁሉ ከታገሰ አላህን ከፈሩትና ከታገሱት ውስጥ ይሆናል።” (እነሆ የሚጠነቀቅና የሚታገስ ሰው (አላህ ይክሰዋል) አላህ የበጎ አድራጊዎችን ዋጋ አያጠፋምና) ምእራፍ ዩሱፍ 90»
መጅሙኡል ፈታዋ 1/133 አዎን በዚያች ብቸኝነት ፤ የምትከጅላት ሴት አለው አለው እያለችህ፤ የውስጥህን ሁሉ ሹክ ልትላት እየጎመጀህ ግን በቃ የአላህ ትልቅነት ሲታወስህ፤ ምንም የማይሰወርበት ተመልካችነቱ ድቅን ሲልብህ ስለዚህም ሁሉንም ለእርሱ ብለህ ስትተው በእርግጠኝነት ታላቅ ሽልማትን ነው ምትጎናፀፈው።አላህ ያግዝህ።

No comments:
Post a Comment