Saturday, 23 August 2014

3 ሴት ልጅ ቤቷ ውስጥ መርጋት

ትምህርት ቁጥር 3

===>ሴት ልጅ ቤቷ ውስጥ መርጋት<===

አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ሴት ልጅ ልትረጋበት የሚገባ ተስማሚ ቦታ ቤቷ እንዲሆን አዟታል ፡፡ ይህን ሲናገር እንዲህ ይላል:-
وَقَرْنَ فِي بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ الْجَاهِلِيَّةِ الْأُولَى [٣٣:٣٣]
«በቤት ውስጥ እርጉ እንደፊተናይቱ መሃይነምነት ጊዜ መገላለጥን አትገላለጡ» (ምእራፍ አል አህዛብ ቁጥር 33)
እዚህ ላይ እንግዲህ አላሁ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ለሴት ልጅ በቤት ውስጥ መርጋትን አዟል ፡: ይህ ሲባል ግን ዘል አለሟን አራት የግድግዳ ማዕዘናት እያየች ትኑር ማለት ፈጽሞ አደለም፡፡ነገር ግን መሰረታዊ መርጊያዋና ስራዋ ቤት ውስት መሆን አለበት ፡፡ይህ የሚጠቁመን ለአስፈላጊ ነገሮች መንቀሳቀስና መውጣት እንደምትችል ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ስለ ሃይማኖቷ ለማወቅ ፤ይህ እንደውም መሰረታዊ እውቀት (ፈርዱልዓይን) ከሆነና ባለችበት ቦታ ሊያስተምራት የሚችል አካል ከሌለ ግዴታ ይሆንባታል ፡፡እንዲሁም ለሌሎች ጉዳይ ከሆነ ዘመናዊ እውቀት ለመገብየት፤ለስራና ለሌሎች ጉዳዮች ክልክላት(ሃራም)ን ርቃና የሌለበት እስከሆነ ድረስ አትከለከልም ፡፡
እዚህ ጋር ግን! በተለይ በተለይ ባለ ትዳር ከሆነች ባሏን መንከባከብና ልጆቿን በትክክለኛ እምነትና ስነምግባር ኮትኩታ ማሳደግ ግዴታ ይሆንባታል ፡፡ስለዚህ ከቤት መውጣተ ለትምህርት ለስራና ለመሳሰሉት ጉዳዮች ከዚህ መሰረት ጋር የሚጋጭ ከሆነ ፍጹም አይፈቀድላትም፡፡ኢስላም በውጭ ጥሮ ግሮ ማምጣትና ቤተሰቡን ማስተዳደር በወንድ ልጅ ላይ የጣለው ሃላፊነት ነው ፡፡ሴት የፈለገ ንብረት አቅም ቢኖራትም ወዳና መርጣ ካላደረገች በስተቀር አትገደድም፡፡እንዲሁም ወልዳ ለምታጠባቸው እራሱ ባሏን ቀጥሮ እንዲያስጠባ መጠየቅ ትችላለት ፡፡ሱብሃነላህ በጣም ይገርማል ከዚህ የበለጠ ልእልነትና ንግስትነት ምን አለ? አላህ ያሳውቀን!!! ውዷ እህቴ ሆይ እባክሽ አስተዋይ ሁኚ ከማንም በላይ ከራስሽም ጭምር እውነተኛና ትክክለኛ ላንቺ የሚገባውን ቦታ ካልነበርሽበት ያስገኘሽና የእርሱን ትዕዛዝ እንድትተገብሪና ከከለከለሽ እንድትርቂ የፈጠረሽ ጌታሽ ጠንቅቆ ያውቃልና ባዘዘሽ ቦታ ላይ ረግተሽ ጥሩ ኢስላማዊ ትውልድን ለመፍጠር ታላቅ ትግል አድርጊ ዲንሽንም በትክክለኛው እና በታዘዝሽው መንገድ እርጂ!!! አላህ ይርዳሽ፡፡

No comments:

Post a Comment