ትምህርት ቁጥር 2
ሙስሊሟ ሴት ከጌታዋ ጋር
ሙስሊሟ ሴትይህን ጸጋ የቸራትን ነጻ ያወጣትን የተሟላና እንከን የለሽ ሃይማኖት የመረጠላትን ታላቁን ጌታዋን ከምንምና ከማንም በፊት አመስጋኝ ትሆናለች፡፡ይህም የሚሆነው እርሱን በብቸኝነት በመገዛት ተውሂድ ይሆናል:: ስግደቷም ጾሟም ፍራቻዋም መመካቷም ተስፋ መከጀሏም ማረድ መሳሏም እንዲሁም ሌሎች ባጠቃላይ የአምልኮ ዘርፎች ፍጹም ለታላቁ ባለውለታዋ ልእሉ ፈጣሪዋ አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ብቻና ብቻ ነው ምታደርገው፡፡ በዚህ ላይ በርሱ አንድንም አካል አታጋራም ፡፡መላኢካም ይሁን ነብይ ጋኔን ይሁን ሷሊህ ዛፍም ይሁን ድንጋይ ፍጹም በራፏ ቁልፍ ነው:: አላህ (ሱብሃነሁወተአላ) እንዲህ ይላል ፡-
قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ لَا شَرِيكَ لَهُ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُسْلِمِينَ
«ስግደቴም መገዛቴም ህይወቴም ሞቴም ለአለማት ጌታ ለአላህ ነው በል ለርሱ ተጋሪ የለውም በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» (ምዕራፍ አል አንዓም 162-163)
አዎ! ይህች እንቁ ሙስሊም ሴት አላሁ (ሱብሃነሁ ወተአላ) እና መልክተኛው (ﷺ) ያዘዙትን በመታዘዝ የከለከሉትን በመከልከልና በመራቅ ትክክለኛ እጅ ሰጪነቷን አልያም ሙስሊምነቷን የምታረጋግጥ ነች:: አላህን (ሱብሃነሁ ወተአላ) ስትገዛ መልክትኛው ባስቀመጡትና በተጔዙበት ምንገድ ብቻ ነው::
የፈጠራ (ቢደአ) አባዜ ያልተጠናወታት ፍጹም መልክተኛውን ተከታይ ናት:: በሁሉም የሂወት ዘርፏ አርአያ የምታደርገው እንቁ ነብዩ(ﷺ)ንና ውድ ባልደረቦቻቸውን (ሰሃባ )ን ብቻ ነው:: ቁርአንና ሱናን በሰሃቦች አልያም በሰለፎች ግንዛቤ ብቻና ብቻ ይዛ ነው ምትጔዘው::በየቀኑ ከዚህ ግንዛቤ ተቃራኒ ሆነው ሚፈለሰፍና ሚፈበረኩ የተዛቡና ስንኩል የሆኑ አመለካከቶች ይሁኑ አንጃዎች ፍጹም አያፍረከርኴትም:: ምክንያቱም የማይሳሳት የማይሰረዝ የማይደለዝ የሆኑትን የቁርአንና ሱናን ብርሃን ይዛ ስለምትጔዝ ነው አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) እንዲህ ይላል :-
أَوَمَن كَانَ مَيْتًا فَأَحْيَيْنَاهُ وَجَعَلْنَا لَهُ نُورًا يَمْشِي بِهِ فِي النَّاسِ كَمَن مَّثَلُهُ فِي الظُّلُمَاتِ لَيْسَ بِخَارِجٍ مِّنْهَا ۚ كَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِلْكَافِرِينَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ [٦:١٢٢]
«ሙት የነበረና ሕያው ያደረግነው ለእርሱም በሰዎች መካከል በእርሱ የሚኼድበትን ብርሃን ያደረግንለት ሰው በጨለማዎች ውስጥ ከርሷ የማይወጣ ኾኖ እንዳልለ ሰው ብጤ ነውን? እንደዚሁ ለከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩት ነገር ተጌጠላቸው፡፡» (ምዕራፍ አል አንአም ቁጥር 122)
ውዷ እህቴ ሆይ ዲንሽን በአግባቡ በመማርና በመረዳት የጌታሽ ትዕዛዝ ለማክበር መጣር ይኖርብሻል! አላህ ይርዳሽ!

No comments:
Post a Comment