Saturday, 23 August 2014

11 ድምጽ መቀየር



ትምህርት ቁጥር 11


ድምጽ መቀየር


አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ለምእመናን እናቶች እና እንዲሁም ከነርሱ በኃላ ለሚመጡት አማኝ ሴቶች እንዲህ ብሏል፤-
يَا نِسَاءَ النَّبِيِّ لَسْتُنَّ كَأَحَدٍ مِّنَ النِّسَاءِ ۚ إِنِ اتَّقَيْتُنَّ فَلَا تَخْضَعْنَ بِالْقَوْلِ فَيَطْمَعَ الَّذِي فِي قَلْبِهِ مَرَضٌ وَقُلْنَ قَوْلًا مَّعْرُوفًا [٣٣:٣٢]
« የነቢዩ ሴቶች ሆይ! ከሴቶች እንደማናቸው አይደላችሁም፡፡ አላህን ብትፈሩ (ትበልጣላችሁ)፡፡ያ በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት እንዳይከጅል በንግግር አትለስልሱም፡፡ መልካምንም ንግግር ተናገሩ፡፡ (33:32)
ድምጽ በተቃራኒ ጾታዎች መካከል ባለው ግንኙነት ከፍተኛ የሆነ ሳቢና ማግኔታዊ ሀይል አለው አንዱን ወደሌላው ጠልፎ የሚይዝ ልዩ ወጥመድ ነው:: አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) አማኝ ሴት መልካምና ቁም ነገሮችን እንጂ ድምጽን በማለሳለስና በማቅለስለስ ወንዶችን ከማማለል እንድትታቀብ ከልክሏታል ፡፡ምክንቱም ይህ ሁኔታ በአዳማጯ ልብ ውስጥ በሽታን ይፈጥራልና ነው፡፡አዎ! ዝሙትን ያስናፍቃል። ለእርሱም ያነሳሳል ይገፋፋል። እዚህ ጋር የድምጽን የአቀየር ስልት በሁለት ከፍለን ልናየው እንችላለን ፡፡
1,ንግግሩን መቀየር ፡-ይህም ማለት አንዲት ሴት ተቃራኒ ጾታን በምታናግርበት ሰአት የተለያዩ የማቆላመጫ ቃላቶችን በመጠቀም ማናገር ነው::
ምሳሌ፡-እከልዬ ስሙን ጠርታ ፣ፍቅሬ ፣ህይወቴና ወዘተ... ይህ ሁኔታ በእውነቱ በቀጥታ መርዝ ነስናሽ አውዳሚ ነገር ነው::
2 በንግግር ውስጥ መለሳለስ፡- ይህ ደግሞ አንዲት ሴት ከተቃራኒ ጾታ ጋር መልካምና ቁም ነገር እያወራች ነገር ግን በውስጡ የምትጠቀማቸው የማለስለስ ፣የመጎተትና የመስለምለም ገጽታዎች ናቸው፡:
ለማንኛውም አንዲት አማኝ ከየትኛውም የፊትና ሙከራዎች አላህን (ሱብሃነሁ ወተአላ) ፈርታ እራሷን ልታቅብ ይገባል፡፡ምስጋና ለአላህ ተገባው፡፡ አትናገሪ አላላትም:: ነገር ግን ድምጷን ተገንና ግርዶ አድርጋ ወንዶችን የፈተናዋ ሰለባ እንዳታደርግ በአጽንኦ ከልክሏታል፡፡ በቃ እጥር ምጥን ቀልጠፍ ቆፍጠን ብሎ መልካምና ቁም ነገሮችን መናገር ዛዛታና እሰጣ ገባ አለመፍጠር:: ሌላው ቁም ነገር ደግሞ እስቲ አንቺ ውዲቷ እህቴ አስተውይ! አላህ እኮ ይህን የከለከለውን መጀመሪያ ያወረደው እጹብ ድንቅ የነብዩ (
) ሚስቶችና የአማኞች እናት በሆኑት እንስቶች ላይ ነው፡፡ታዲያ እኔና አንቺስ በምን መልኩ ነው መሆን የሚገባን??? እራስን መሸንገል አያዛልቅም:: ይልቁንም ያሉ ግድፈቶችንና መጥፎ ዝንባሌዎችን አርሞ ማስተካከል የብልህ ሰዎች መገለጫ ነው::



10 በጫማ መሬትን መምታት



                         ትምህርት ቁጥር

          
●▬▬▬▬▬▬▬▬۩۞۩●▬▬▬▬▬▬▬▬●
                        በጫማ መሬትን መምታት
          
●▬▬▬▬▬▬▬▬۩۞۩●▬▬▬▬▬▬▬▬●
 

በጫማ መሬትን መምታት
እንደሚታወቀው በተቃራኒ ጾታዎች መካከል ያለው ስሜት ግለትና ተነሳሽነቱ ረቂቅ በሆነ መንገድ ነው:: ታዲያ አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) የፈጠረውን አዋቂ ነውና በዚህ በረቂቅ መልኩ እንኳ ሳይቀር ተቀስቅሰው ወደ ውድመት ሊወስዱ የሚችሉ በሮችን ሁሉ ዘግቷል:: ከዚህም ውስጥ ሴትን ልጅ ወንዱን ለማማለልና እይታውን ለመሳብ በምትራመድበት ጫማ ላይ የምታደርገው የእዩኝ ጥሪና ድምጽን እንዳታደርግ መከልከሉ ነው:: አዎ! አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ከዚህ ድርጊት እንድትታቀብ አዟታል እርሷም ይህንን ያለ ድርድር ፈጻሚ መሆን ይጠበቅባታል:: የአላህን ትእዛዝ አሻፈረኝ ብለው ስሜታቸውን ከሚከተሉት አመጸኞች መመደብ የለባትም:: እነርሱ በየቀኑ ለዚህ ከንቱ አላማ የሚሆናቸውን ጫማ ለመግዛት በየሱቁ ሲንከራተቱ ይስተዋላሉ:: አረ አሁን አሁንማ አንዳንድ ሴቶች የሚጫሙት ጫማ እርዝመት በሜትርም ሳይለካ የሚቀር አመስለኝም ይህን ተጫምተው በሚራመዱበት ሰአት ደግሞ ፍጹም ተወዛዋዥና ዳንሰኛ እንጂ ከቶም ተራማጅ አይመስሉም:: ይገርማል እኮ ጃል:: ከአላህም ጋር ተጣልተው በገዛ ገንዘባቸው በሽታም ሸምተው:: ምክንያቱም በህክምናውም ጥናት እንደተደረሰበት ተረከዙ የረዘመ(ታኮ) ጫማ መጫማት የሰውነት ክብደት ቀጥታ የሚያርፈው እርሱ ላይ ስለሆነ ኩላሊት ለመታመምና መሰል በሽታዎች ይጋለጣሉ:: አላህ ይጠብቀን::



9 ኒቃቤ



ትምህርት ቁጥር 9

#ኒቃቤ

ኒቃቤ

አዎ እንቁ ነኝ ሽልምልም በኒቃቤ ኩሩ
ጠላት ቢንገበገብ ቢቆጩብኝ ቢያሩ
ድንጋይን ፈንቅለው ጉድጓድ ቢቆፍሩ
ይመክትልኛል አልዩ ከቢሩ
ሰሚ ነኝ ታዛዥ ነኝ ጌታዬን አፍቃሪ
ነብዬን ተከታይ በሱናቸው ሰሪ
ይህ ነው መሰረቴ የመኖሬ አላማ
አላህን ብቻ ማምለክ በዱንያው አውድማ
ነገ እንዳጭድበት የአኼራን ምንዳ
ፍጻሜዩ እንዳይበላሽ እንዳይሆን ነዳማ
ኒቃብ መማሬን አያቅብ መስራቴን አይገታ
ሀራም ከሌለበት ድብልቅ ጋጋታ
አዎ አበርካች ነኝ መልካም አስተዋጾ
ትውልዶችን መልማይ በኢስላም አንጾ
ይህን የቸረኝ አምላክ ምስጋና ተገባው
እኔስ ተደነኩኝ ለታላቅ ልእልናው!
--------------
በእውነቱ በርግጠኝነት ያለጥርጥር አርአያዋ ሞናሊዛና ዲያና ያልሆኑ ይልቁኑም ኸድጃና አዒሻን ያደረገች አንዲት አማኝ ኒቃብ ለባሽ ብቻ ሳትሆን ኒቃብ በመልበሷ በእጅጉ የረካችና ደስተኛ ነች፡፡ ምክንቱም:- ሞዴል ያደረገቻቸው እጹብ ድንቅ የአለማችን ሴቶች (ሰሀብያት) ይህ ነበር መገለጫና መለያቸው ፡፡በነበራቸው የሕይወት ጉዞ ላይ በኒቃብ ሊደራደሩ ቀርቶ ታላቁ የአምልኮት ስርአት የሆነውን ኡምራና ሃጅ ላይ እንኳ ሳይቀር የነበራቸውን የማይነጥፍና ጽኑ አቌም እናታችን አዒሻ (ረድየላሁ አንሀ) እንዲህ ስትል ገልጻዋለች {ከአላህ ከመልክተናው (
) ጋር ኢህራም (የሃጅና ኡምራ) የአምልኮ ስርአት ላይ ሆነን ሳለ ተጔዦች ባጠገባችን ያልፉ ነበር እኛም ከራሳችን ላይ ያለውን ጉፍታ ወደ ፊታችን እንለቀዋለን::ሲያልፉ ደግሞ እንገልጠዋለን}´
እንግዲህ አንቺ ውዲቷ እህቴ እነርሱ በዚያ ታላቅ የአምልኮ ስርአት ላይ ይህ ከነበረ አቌማቸው እኔና አንቺስ??? መልሱን ለአማኟ እህቴ ትቻለሁ:: በሚገባና በትክክል እንደምትመልሺው በጌታዬ ላይ ባለሙሉ ተስፈኛ ነኝ::


ትምህርት ቁጥር 15

#ኒቃቤ

ኒቃቤ

አዎ እንቁ ነኝ ሽልምልም በኒቃቤ ኩሩ
ጠላት ቢንገበገብ ቢቆጩብኝ ቢያሩ
ድንጋይን ፈንቅለው ጉድጓድ ቢቆፍሩ
ይመክትልኛል አልዩ ከቢሩ
ሰሚ ነኝ ታዛዥ ነኝ ጌታዬን አፍቃሪ
ነብዬን ተከታይ በሱናቸው ሰሪ
ይህ ነው መሰረቴ የመኖሬ አላማ
አላህን ብቻ ማምለክ በዱንያው አውድማ
ነገ እንዳጭድበት የአኼራን ምንዳ
ፍጻሜዩ እንዳይበላሽ እንዳይሆን ነዳማ
ኒቃብ መማሬን አያቅብ መስራቴን አይገታ
ሀራም ከሌለበት ድብልቅ ጋጋታ
አዎ አበርካች ነኝ መልካም አስተዋጾ
ትውልዶችን መልማይ በኢስላም አንጾ
ይህን የቸረኝ አምላክ ምስጋና ተገባው
እኔስ ተደነኩኝ ለታላቅ ልእልናው!
--------------
በእውነቱ በርግጠኝነት ያለጥርጥር አርአያዋ ሞናሊዛና ዲያና ያልሆኑ ይልቁኑም ኸድጃና አዒሻን ያደረገች አንዲት አማኝ ኒቃብ ለባሽ ብቻ ሳትሆን ኒቃብ በመልበሷ በእጅጉ የረካችና ደስተኛ ነች፡፡ ምክንቱም:- ሞዴል ያደረገቻቸው እጹብ ድንቅ የአለማችን ሴቶች (ሰሀብያት) ይህ ነበር መገለጫና መለያቸው ፡፡በነበራቸው የሕይወት ጉዞ ላይ በኒቃብ ሊደራደሩ ቀርቶ ታላቁ የአምልኮት ስርአት የሆነውን ኡምራና ሃጅ ላይ እንኳ ሳይቀር የነበራቸውን የማይነጥፍና ጽኑ አቌም እናታችን አዒሻ (ረድየላሁ አንሀ) እንዲህ ስትል ገልጻዋለች {ከአላህ ከመልክተናው (
) ጋር ኢህራም (የሃጅና ኡምራ) የአምልኮ ስርአት ላይ ሆነን ሳለ ተጔዦች ባጠገባችን ያልፉ ነበር እኛም ከራሳችን ላይ ያለውን ጉፍታ ወደ ፊታችን እንለቀዋለን::ሲያልፉ ደግሞ እንገልጠዋለን}´
እንግዲህ አንቺ ውዲቷ እህቴ እነርሱ በዚያ ታላቅ የአምልኮ ስርአት ላይ ይህ ከነበረ አቌማቸው እኔና አንቺስ??? መልሱን ለአማኟ እህቴ ትቻለሁ:: በሚገባና በትክክል እንደምትመልሺው በጌታዬ ላይ ባለሙሉ ተስፈኛ ነኝ::